ዘዳግም 1:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እግዚአብሔርም የቃላችሁን ድምፅ ሰምቶ ተቈጣ፤ እንዲህም ብሎ ማለ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም እናንተ ያላችሁትን በሰማ ጊዜ ተቈጣ፤ ማለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታም የቃላችሁን ድምፅ ሰምቶ ተቆጣም፤ እንዲህም ሲል ማለ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔርም የማጒረምረም ጩኸታችሁን ሰምቶ ተቈጣ፤ ስለዚህም እንዲህ ሲል ማለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የቃላችሁን ድምፅ ሰምቶ ተቆጣ፦ |
ወተትና ማርም ወደምታፈስሰው ከምድር ሁሉ ወደምታምር ወደ ሰጠኋቸው ምድር እንዳላገባቸው በምድረ በዳ በእነርሱ ላይ ፈጽሜ እጄን አነሣሁ።
እነሆም፥ የእግዚአብሔርን መዓት በእስራኤል ላይ አብዝታችሁ ትጨምሩ ዘንድ እናንተ በኀጢአተኞች ሰዎች በደል በአባቶቻችሁ ፋንታ ተነሥታችኋል።