ልናገርም እንደሚገባኝ እገልጠው ዘንድ ጸልዩልኝ።
ደግሞም መናገር እንደሚገባኝ ቃሉን በግልጽ እንድናገር ጸልዩልኝ።
ቃሉንም መናገር እንደሚገባኝ ያህል ለመግለጥ እንድችል ጸልዩልኝ።
እኔም እንደሚገባኝ ቃሉን በግልጥ እንድናገር ጸልዩልኝ።
ልናገር እንደሚገባኝ ያህል እገልጠው ዘንድ ጸልዩልኝ።
አሁንም አቤቱ፥ ትምክህታቸውን ተመልከት፤ ቃልህንም በግልጥ ያስተምሩ ዘንድ ለባሮችህ ስጣቸው።
ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው እንዲህ አሉአቸው፥ “ለሰው ከመታዘዝ ይልቅ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይገባል።
እንግዲህ ይህን ያህል ተስፋ ካለን በግልጥ ፊት ለፊት ልንቀርብ እንችላለን።
ስለ ወንጌልም በእስራት መልእክተኛ የሆንሁ፦ መናገር እንደሚገባኝ ስለ እርሱ በግልጥ እናገር ዘንድ ጸልዩ።
ዘመኑን እየዋጃችሁ ከሃይማኖት ወደ ተለዩ ሰዎች በማስተዋል ሂዱ።
ለእያንዳንዱ እንዴት እንደምትመልሱ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ በጨው እንደ ተቀመመ በጸጋ ይሁን።