ቈላስይስ 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮስጦስ የተባለ ኢያሱም፥ ከግዙራን ሰዎች ወገን የሚሆኑ እነዚህ ሰላም ይሏችኋል። በእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ ረዳቶች እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እነርሱም እኔን አጽናንተውኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮስጦስ የተባለው ኢያሱም ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ከተገረዙት መካከል ለእግዚአብሔር መንግሥት ዐብረውኝ የሚሠሩት፣ እኔንም ያጽናኑኝ እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እነርሱም አጽናንተውናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮስጦስም የተባለ ኢያሱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ ከተገረዙትም ወገን የሆኑ፥ በእግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩት እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እኔንም አጽናንተውኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮስጦስ ተብሎም የሚጠራው ኢያሱ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው ከሚሠሩት ሰዎች መካከል የአይሁድ ወገኖች የሆኑት እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እኔንም አጽናንተውኛል። |
ለተገዘሩትም አባት ይሆን ዘንድ ነው፤ ነገር ግን ለተገዘሩት ብቻ አይደለም፤ እርሱ አባታችን አብርሃም ሳይገዘር እንደ አመነ ሳይገዘሩ የአባታችን የአብርሃምን የሃይማኖቱን ፍለጋ ለሚከተሉ ደግሞ ነው እንጂ።
ከእርሱም ጋር አብረን እየሠራን፥ የተቀበላችኋትን የእግዚአብሔር ጸጋ ለከንቱ እንዳታደርጓት እንማልዳችኋለን።
እናንተ አሕዛብ አስቡ፤ ቀድሞ በሥጋ ሥርዐት ነበራችሁ፤ ያልተገዘሩም ይሉአችሁ ነበር፤ እንዲህ የሚሉአችሁም የተገዘሩ ሰዎች ናቸው፤ ግዝረት ግን በሥጋ ላይ የሚደረግ የሰው እጅ ሥራ ነው።
ወንድሜና አጋዤ ስትሪካ ሆይ፥ እንድትረዳቸው አንተንም እለምንሃለሁ፤ ወንጌልን በማስተማር ከቀሌምንጦስና ሥራቸው ከተባበረ፥ ስማቸውም በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፈላቸው ከወንድሞቻችንም ሁሉ ጋር ከእኔም ጋር ደክመዋልና።
ስለ እምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ ወንድማችንን የእግዚአብሔርንም አገልጋይ ከእኛ ጋርም አብሮ በክርስቶስ ወንጌል የሚሠራውን ጢሞቴዎስን ላክነው፤