La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ቈላስይስ 1:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሁሉ​ንም በእ​ርሱ ይቅር ይለው ዘንድ በመ​ስ​ቀሉ ባፈ​ሰ​ሰው ደም በም​ድ​ርና በሰ​ማ​ያት ላሉ ሰላ​ምን አደ​ረገ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው ደሙ ሰላምን በማድረግ፣ በምድርም ሆነ በሰማይም ያለውን ነገር ሁሉ በርሱ በኩል ከራሱ ጋራ አስታረቀ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በመስቀሉም ደም ሰላምን በማድረግ በሰማይም ሆነ በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ በእርሱ አማካይነት ከራሱ ጋር አስታርቋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በእርሱም አማካይነት በሰማይም ሆነ በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ ከራሱ ጋር አስታረቀ፤ በመስቀል ላይ በፈሰሰው በልጁ ደምም ሰላምን አደረገ።

Ver Capítulo



ቈላስይስ 1:20
22 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ለማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ይሆን ዘንድ ከደሙ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን የሚ​ገ​ባው የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ አይ​በ​ላም፤ በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላል።


አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።


ይህም ለሰላም ይሆናል፥ አሦራዊውም ወደ አገራችን በገባ ጊዜ፥ ምድራችንንም በረገጠ ጊዜ ሰባት እረኞችና ስምንት አለቆች እናስነሣበታለን።


ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ሁለት ጊደ​ሮች፥ አም​ስት አውራ በጎች፥ አም​ስት አውራ ፍየ​ሎች፥ አም​ስት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ የጋ​ዴ​ዮን ልጅ የአ​ቢ​ዳን መባ ይህ ነበረ።


ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።”


“ክብር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማ​ያት፥ ሰላ​ምም በም​ድር፥ ለሰው ልጅም በጎ ፈቃድ ሆነ” ይሉ ነበር።


ቆር​ኔ​ሌ​ዎ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “የዛሬ አራት ቀን በዘ​ጠኝ ሰዓት በዚች ሰዓት በቤቴ ስጸ​ልይ የሚ​ያ​ን​ፀ​ባ​ርቅ ልብስ የለ​በሰ አንድ ሰው በፊቴ ቆሞ ታየኝ።


እን​ግ​ዲህ በእ​ም​ነት ከጸ​ደ​ቅን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሰላ​ምን እና​ገ​ና​ለን።


የሚ​ደ​ር​ስ​በ​ት​ንም ጊዜ​ውን ወሰነ፤ በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያለ​ውም ሁሉ ይታ​ደስ ዘንድ ክር​ስ​ቶ​ስን በሁሉ ላይ አላ​ቀው።


ይህም በሰ​ማ​ይና በም​ድር በቀ​ላ​ያ​ትና ከም​ድር በታች ያለ ጕል​በት ሁሉ ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ይሰ​ግድ ዘንድ ነው።


በእ​ርሱ ቃል​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን ፈጥ​ሮ​አ​ልና በሰ​ማይ ያለ​ውን፥ በም​ድ​ርም ያለ​ውን፥ የሚ​ታ​የ​ው​ንና የማ​ይ​ታ​የ​ውን፥ መና​ብ​ር​ትም ቢሆኑ፥ አጋ​እ​ዝ​ትም ቢሆኑ፥ መኳ​ን​ን​ትም ቢሆኑ፥ ቀደ​ም​ትም ቢሆኑ፥ ሁሉን በእ​ርሱ ቃል​ነት ፈጥ​ሮ​አ​ቸ​ዋ​ልና፤ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእ​ርሱ ለእ​ርሱ ተፈ​ጠረ፤


ስለ​ዚ​ህም የሕ​ዝ​ብን ኀጢ​አት ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሆ​ነው ነገር ሁሉ የሚ​ም​ርና የታ​መነ ሊቀ ካህ​ናት እን​ዲ​ሆን በነ​ገር ሁሉ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሊመ​ስል ተገ​ባው።