“በምድር ላይም ራብ፥ ወይም ቸነፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረማሞ ቢሆን፥ አንበጣ፥ ወይም ኩብኩባ ቢመጣ፥ የሕዝብህም ጠላት ከከተሞቻቸው በአንዲቱ ከብቦ ቢያስጨንቃቸው፥ መቅሠፍትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥
አሞጽ 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአባርና በቸነፈር መታኋችሁ፤ አትክልታችሁ፥ ወይናችሁና በለሳችሁ፥ ወይራችሁም ከበጀ በኋላ ተምች በላው፤ ይህም ሆኖ እናንተ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የአትክልትና የወይን ቦታዎቻችሁን ብዙ ጊዜ መታሁ፤ በዋግና በአረማሞም አጠፋኋቸው፤ አንበጦችም የበለስና የወይራ ዛፎቻችሁን በሉ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በዋግና በአረማሞ መታኋችሁ፤ የአታክልቶቻችሁንም ብዛት ወይኖቻችሁንም በለሶቻችሁንም ወይራዎቻችሁንም ተምች በላው፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰብላችሁን የሚያደርቅ ብርቱ ነፋስ ላክሁባችሁ፤ አትክልታችሁንና የወይን ተክላችሁን የበለስና የወይራ ዛፋችሁን ሁሉ አንበጣ በላው፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዋግና በአረማሞ መታኋችሁ፥ የአታክልቶቻችሁንም ብዛት ወይኖቻችሁንም በለሶቻችሁንም ወይራዎቻችሁንም ተምች በልቶአል፥ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር። |
“በምድር ላይም ራብ፥ ወይም ቸነፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረማሞ ቢሆን፥ አንበጣ፥ ወይም ኩብኩባ ቢመጣ፥ የሕዝብህም ጠላት ከከተሞቻቸው በአንዲቱ ከብቦ ቢያስጨንቃቸው፥ መቅሠፍትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥
“በምድር ላይ ራብ፥ ወይም ቸነፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረማሞ፥ ወይም አንበጣ፥ ወይም ኩብኩባ ቢሆን፥ ጠላቶቻቸውም የሀገሩን ከተሞች ከብበው ቢያስጨንቁአቸው፥ ማናቸውም መቅሠፍትና ደዌ ቢሆን፥
እነሆ፥ እሳት የምታነድዱ፥ የእሳትንም ነበልባል ከፍ ያደረጋችሁ ሁላችሁ፥ በእሳታችሁ ብርሃንና ባነደዳችሁት ነበልባል ሂዱ፤ ስለ እኔ ይህ ይሆንባችኋል፤ በኀዘንም ትተኛላችሁ።
ጠላቶቹን ሶርያውያንንም ከምሥራቅ፥ አረማውያንንም ከምዕራብ ያንቀሳቅስበታል፤ እስራኤልንም በተከፈተ አፍ ይበሉታል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
አቤቱ! ዐይኖችህ ለሃይማኖት አይደሉምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል፤ ነገር ግን አላዘኑም፤ ቀጥቅጠሃቸውማል፤ ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱም ዘንድ እንቢ አሉ።
“በከተማችሁ ሁሉ ጥርስን ማጥረስን፥ በስፍራችሁም ሁሉ እንጀራን ማጣትን ሰጠኋችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም ይላል እግዚአብሔር።
የሁለት ወይም የሦስት ከተሞች ሰዎች ወደ አንዲት ከተማ ውኃ ይጠጡ ዘንድ ሄዱ፤ ነገር ግን አልረኩም፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።
ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥
ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፣ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር በክሳት፥ በንዳድም፥ በጥብሳትም፥ በትኵሳትም፥ በድርቅም፥ በዋግም፥ በአረማሞም ይመታሃል፤ እስክትጠፋም ድረስ ያሳድዱሃል።