አሞጽ 3:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይስ አንበሳ የሚነጥቀው ነገር ሳያገኝ በጫካው ውስጥ በከንቱ ያገሣልን? ወይስ የአንበሳ ደቦል አንዳች ሳይዝ በመደቡ ሆኖ በከንቱ ይጮኻልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንበሳ የሚበላውን ሳያገኝ፣ በጫካ ውስጥ ይጮኻልን? ምንም ነገርስ ሳይዝ፣ በዋሻው ውስጥ ያገሣልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይስ አንበሳ የሚነጥቀው ነገር ሳያገኝ በጫካ ውስጥ ያገሣልን? ወይስ የአንበሳ ደቦል አንዳች ነገር ሳይዝ በማደርያው ሆኖ ይጮኻልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንበሳ በደን ውስጥ ዐድኖ የሚበላውን ሳያገኝ በከንቱ ያገሣልን? የአንበሳ ደቦልስ አንዳች ነገር ዐድኖ ሳይዝ በሚኖርበት ቦታ ድምፁን ያሰማልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይስ አንበሳ የሚነጥቀው ነገር ሳያገኝ በጫካ ውስጥ ያገሣልን? ወይስ የአንበሳ ደቦል አንዳች ሳይዝ በመደቡ ሆኖ ይጮኻልን? |
ጌታ እግዚአብሔርን እከተለው ዘንድ እሄዳለሁ፤ እርሱ ያድነናልና፤ እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፤ የውኃ ልጆችም ይደነግጣሉ።
እኔም ለኤፍሬም እንደ ነብር፥ ለይሁዳም ቤት እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁና፤ እኔም ነጥቄ እሄዳለሁ፤ እወስድማለሁ፤ የሚያድናቸውም የለም።
እንዲህም አለ፥ “እግዚአብሔር ከጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይናገራል፤ ከኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል፤ የእረኞችም ማሰማሪያዎች ያለቅሳሉ፤ የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።”
ወይስ ወፍ፥ አጥማጅ ከሌለው፥ በምድር ላይ በወጥመድ ይያዛልን? ወይስ ወስፈንጠር አንዳች ሳይዝ ከምድር በከንቱ ይፈናጠራልን?