አሞጽ 3:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በፊቷ የሚመጣባትን አላወቀችም፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በሀገራቸው ቅሚያንና ግፍን የሚያከማቹ ናቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ቅሚያንና ዝርፊያን በምሽጋቸው ውስጥ የሚያከማቹ፣ በጎ ነገር ማድረግን አያውቁም፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በንጉሥ ቅጥሮቻቸውም ግፍንና ቅሚያን የሚያከማቹ ቅን ነገር እንዴት እንደሚደረግ አያውቁም፥” ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነዚህ ሕዝቦች መልካም ነገር ማድረግን አያውቁም፤ በዐመፅና በግፍ በተወሰደ ንብረት ምሽጋቸውን ይሞላሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ግፍንና ቅሚያን በአዳራሾቻቸው የሚያከማቹት ቅን ነገርን ያደርጉ ዘንድ አያውቁም፥ ይላል እግዚአብሔር። |
ደግ ሴት ለባሏ ክብርን ታስገኛለች፥ ጽድቅን የምትጠላ ሴት ግን የውርደት ወንበር ናት። ሐኬተኞች ከብልጽግና ይደኸያሉ፥ ብርቱዎች ግን ብልጽግናን ይከተላሉ።
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሓይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ ነበረ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ በሚገፉአቸውም እጅ ኀይል ነበረ። እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።
የሕዝቤ አለቆች አላወቁኝም፤ እነርሱ ሰነፎች ልጆች ናቸው፤ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፤ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።
እኔም እንዲህ አልሁ፥ “የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ፍርድ አላወቁምና እነዚህ በእውነት ድሆችና ደካሞች ናቸው፤
ሰውንም ባያስጨንቅ፥ ለባለ ዕዳም መያዣውን ቢመልስ፥ ፈጽሞም ባይቀማ፥ ከእንጀራውም ለተራበ ቢሰጥ፥ የተራቈተውንም ከልብሱ ቢያለብስ፤
እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን አይተሃልን? በዚህ የሚያደርጉትን ይህን ኀጢአት ያደርጉ ዘንድ ለይሁዳ ቤት ጥቂት ነገር ነውን? ምድሪቱን በኀጢአት ሞልተዋታል፤ ያስቈጡኝም ዘንድ ተመልሰዋል፤ እነሆም ቅርንጫፉን አስረዝመዋል። ይዘባበታሉም።
በሐሰት አድርገዋልና፥ ሌባም ገብቶአልና፥ በውጭም ወንበዴዎች ቀምተዋልና እስራኤልን እፈውስ ዘንድ በወደድሁ ጊዜ የኤፍሬም ኀጢአትና የሰማርያ ክፋት ተገለጠ።
በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ፥ ድሆችንም የምትበድሉ፥ ችግረኞችንም የምታስጨንቁ፥ ጌቶቻቸውንም፦ አምጡ እንጠጣ የምትሉ እናንተ የባሳን ላሞች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ።
ፍርድን ወደ ቍጣ፥ የእውነትንም ፍሬ ወደ እሬት ለውጣችኋልና፥ በውኑ ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን? ወይስ በሬዎች በዚያ ላይ ያርሳሉን?
ጌታ እግዚአብሔር፥ “የያዕቆብን ትዕቢት አረክሳለሁ፤ ሀገሮቹንም ጠላሁ፤ ከተሞቹንም ከሚኖሩባቸው ሰዎች ጋር አጠፋለሁ” ብሎ በራሱ ምሎአልና።