አሞጽ 2:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሞዓብ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፤ የከተሞችዋንም መሠረቶች ትበላለች፤ ሞዓብም በድካምና በውካታ፥ በመለከትም ድምፅ ይሞታል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቂርዮትን ምሽጎች እንዲበላ፣ በሞዓብ ላይ እሳት እሰድዳለሁ፤ ሞዓብ በጦርነት ጩኸትና በመለከት ድምፅ መኻል፣ በታላቅ ሁካታ ውስጥ ይሞታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሞዓብ ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የቂርዮትንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፤ ሞዓብም በውካታና በጩኸት በመለከትም ድምፅ መካከል ይሞታል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በሞአብ ምድር እሳት እለቅበታለሁ፤ የቂሪዮትንም ምሽጎች ያቃጥላል፤ ጦረኞች ድንፋታ፥ ጩኸትና የመለከት ድምፅ እያሰሙ የሞአብን ሕዝብ ይጨርሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሞዓብ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ የቂርዮትንም አዳራሾች ትበላለች፥ ሞዓብም በውካታና በጩኸት በመለከትም ድምፅ ይሞታል፥ |
ከሐሴቦን ጩኸት እስከ ኤሊያሊና እስከ ኢያሳ ድረስ ድምፃቸውን ሰጥተዋል፤ ከሴጎር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ይደርሳል፤ የኔምሬም ውኃ ደርቋልና።
ከሰልፍ የሸሹ ከሐሴቦን ጥላ በታች ቆመዋል፤ እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሴዎን ወጥቶአል፤ የሞአብንም ማዕዘን፥ የሚጮኹ ልጆችንም ራስ በልቶአል።
በራባ ቅጥር ላይ እሳትን አነድዳለሁ፤ በጦርነት ቀን በጩኸት መሠረቶችዋን ትበላለች፤ በፍጻሜዋም ቀን ትናወጣለች።