ሐዋርያት ሥራ 8:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጃንደረባውም ለፊልጶስ መልሶ፥ “ነቢዩ ስለ ማን እንዲህ ይላል? ስለ ራሱ ነውን? ወይስ ስለ ሌላ? እባክህ ንገረኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጃንደረባውም መልሶ ፊልጶስን፣ “ነቢዩ ይህን የሚናገረው ስለ ማን ነው? ስለ ራሱ ነው ወይስ ስለ ሌላ ሰው? እባክህ ንገረኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጃንደረባውም ለፊልጶስ መልሶ “እባክህ፥ ነቢዩ ይህን ስለ ማን ይናገራል? ስለ ራሱ ነውን ወይስ ስለ ሌላ?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጃንደረባውም ፊልጶስን፥ “ነቢዩ ይህን የተናገረው ስለ ማን ነው? ስለ ራሱ ነውን ወይስ ስለሌላ? እባክህን ንገረኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጃንደረባውም ለፊልጶስ መልሶ፦ “እባክህ፥ ነቢዩ ይህን ስለ ማን ይናገራል? ስለ ራሱ ነውን ወይስ ስለ ሌላ?” አለው። |
ተነሥቶም ሄደ፤ እነሆም፥ የኢትዮጵያ ንግሥት የሕንደኬ ጃንደረባ ከሹሞችዋ የበለጠ፥ በሀብቷም ሁሉ ላይ በጅሮንድ የነበረ፥ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ነበር፤ እርሱም ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።