ሐዋርያት ሥራ 8:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመራራ መርዝ ተመርዘህ፥ በዐመፃ ማሰሪያ ተተብትበህ የምትኖር ሆነህ አይሃለሁና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም በመራራነት ተሞልተህ፣ በዐመፅ ሰንሰለት ተይዘህ አይሃለሁና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመራራ መርዝና በዐመፅ እስራት እንዳለህ አይሃለሁና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ በመራራ ቅናት እንደ ተሞላህና የኃጢአት እስረኛ እንደ ሆንክ አያለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመራራ መርዝና በዓመፅ እስራት እንዳለህ አይሃለሁና።” |
አሁንም በምድር ሁሉ ላይ የሚያደርገውን ያለቀና የተቈረጠ ነገርን ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰምቻለሁና እስራታችሁ እንዳይጸናባችሁ እናንተ ደስ አይበላችሁ።
ይህን ጾም የመረጥሁ አይደለም ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን የበደልን እስራት ፍታ፤ ጠማማውን ሁሉ አቅና፤ የተጨነቀውንም ሁሉ አድን፤ የዐመፃ ደብዳቤንም ተው።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ይህን ሕዝብ መከራን አበላዋለሁ፤ የሐሞትንም ውኃ አጠጣዋለሁ።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ኀጢኣትን የሚሠራ ሁሉ የኀጢኣት ባርያ ነው።
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።
አስተውሉ፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ የሚያቃልል አይኑር፤ ሕማምን የምታመጣ፥ ብዙዎችንም የምታስታቸውና የምታረክሳቸው መራራ ሥር የምትገኝበትም አይኑር።