እግዚአብሔርም አብራምን አለው፥ “ዘርህ ለእነርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ ዕወቅ፤ አራት መቶ ዓመታትም ባሪያዎች አድርገው ይገዙአቸዋል፤ ያሠቃዩአቸዋል፤ ያስጨንቋቸዋልም።
ሐዋርያት ሥራ 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፦ ‘ዘርህ በባዕድ ሀገር መጻተኞች ሆነው ይኖራሉ፤ አራት መቶ ዓመትም ባሮች አድርገው ይገዙአቸዋል፤ መከራም ያጸኑባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናገረው፤ ‘ዘርህ በባዕድ አገር መጻተኛ ይሆናል፤ አራት መቶ ዓመትም በባርነት ተረግጦ ይገዛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ዘሩ በሌላ አገር መጻተኞች እንዲሆኑ አራት መቶ ዓመትም ባርያዎች እንዲያደርጉአቸው እንዲያስጨንቁአቸውም እንዲህ ተናገረ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘሩም በባዕድ አገር ስደተኛ ሆኖ እንደሚኖርና በዚያም አገር አራት መቶ ዓመት ባሪያ አድርገው በጭቈና እንደሚገዙት ነግሮት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ዘሩ በሌላ አገር መጻተኞች እንዲሆኑ አራት መቶ ዓመትም ባሪያዎች እንዲያደርጉአቸው እንዲያስጨንቁአቸውም እንዲህ ተናገረ፤ |
እግዚአብሔርም አብራምን አለው፥ “ዘርህ ለእነርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ ዕወቅ፤ አራት መቶ ዓመታትም ባሪያዎች አድርገው ይገዙአቸዋል፤ ያሠቃዩአቸዋል፤ ያስጨንቋቸዋልም።
እንግዲህ እንዲህ እላለሁ፦ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ይህ ኪዳን ጽኑዕ ነው፤ ከዚህም በኋላ በአራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኦሪት መጣች፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ልትከለክል አይደለም።