ሐዋርያት ሥራ 7:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእስራኤልም ልጆች፦ ‘እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋልና እርሱን ስሙት’ ያላቸው ይህ ሙሴ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእስራኤልንም ልጆች፣ ‘እግዚአብሔር እንደ እኔ ያለ ነቢይ ከወንድሞቻችሁ መካከል ያስነሣላችኋል’ ያላቸው ይኸው ሙሴ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ሰው ለእስራኤል ልጆች ‘እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል፤ እርሱን ስሙት፤’ ያላቸው ሙሴ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ጌታ አምላካችሁ እኔን እንዳስነሣኝ እንዲሁ ከወንድሞቻችሁ መካከል ነቢይ ያስነሣላችኋል’ ብሎ ለእስራኤላውያን የተናገረው ይኸው ሙሴ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ ሰው ለእስራኤል ልጆች፦ ‘እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል፤ እርሱን ስሙት’ ያላቸው ሙሴ ነው። |
ጲላጦስም፥ “እንግዲያ አንተ ንጉሥ ነህን?” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ራስህ ትላለህ፤ እኔ ስለዚህ ተወለድሁ፤ ስለዚህም ለእውነት ልመሰክር ወደ ዓለም መጣሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰማኛል” አለው።
በምድረ በዳ በማኅበሩ መካከል የነበረ እርሱ ነው፤ በደብረ ሲና ከአነጋገረው መልአክና፤ ከአባቶቻችንም ጋር ለእኛ ሊሰጠን የሕይወትን ቃል የተቀበለ እርሱ ነው።