ሐዋርያት ሥራ 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም ከሆነ ከሦስት ሰዓት በኋላ ሚስቱ መጣች፤ ባልዋም የሆነውን ሳታውቅ ገባች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሦስት ሰዓት ያህልም ካለፈ በኋላ፣ ሚስቱ የሆነውን ሳታውቅ መጥታ ገባች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሦስት ሰዓት ያህል በኋላም ሚስቱ የሆነውን ሳታውቅ ገባች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሦስት ሰዓት ያኽል በኋላ የሐናንያ ሚስት በባልዋ ላይ የደረሰውን ሁናቴ ሳታውቅ መጣች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሦስት ሰዓት ያህል በኋላም ሚስቱ የሆነውን ሳታውቅ ገባች። |
ጴጥሮስም፥ “እስኪ ንገሪኝ፥ መሬታችሁን የሸጣችሁት ይህን ለሚያህል ነውን?” አላት፤ እርስዋም፥ “አዎን፥ እንዲሁ ነው” አለች።