እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሠዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን።
ሐዋርያት ሥራ 5:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐናንያ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ሚስቱም ሰጲራ ትባል ነበር፤ መሬቱንም ሸጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐናንያ የተባለ ሰው፣ ከሚስቱ ከሰጲራ ጋራ መሬት ሸጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐናንያም የተባለ አንድ ሰው ሰጲራ ከተባለች ከሚስቱ ጋር መሬት ሸጠ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐናንያ የሚባል አንድ ሰው ሰጲራ ከምትባለው ሚስቱ ጋር ሆኖ መሬት ሸጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐናንያም የተባለ አንድ ሰው ሰጲራ ከተባለች ከሚስቱ ጋር መሬት ሸጠ፥ |
እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሠዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን።
ከሚስቱም ጋራ ተማክሮ የዋጋዉን እኩሌታ አስቀረ፤ የዋጋውንም እኩሌታ አምጥቶ በሐዋርያት እግር አጠገብ አስቀመጠ።
በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፤ እኵሌቶቹም ለክብር፥ እኵሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤
በዘንበሪም ወገን ምልክት ታየ፤ የዘንበሪም ቤተ ሰብ እያንዳንዱ ተለየ፤ ከይሁዳም ወገን በሆነ በከርሚ ልጅ በዘንበሪ ልጅ በዛራ ልጅ በአካን ላይ ምልክት ታየ።