ሐዋርያት ሥራ 4:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊቀ ካህናቱ ሐና፥ ቀያፋም፥ ዮሐንስና እለእስክንድሮስም፥ የሊቀ ካህናቱም ወገን ሁሉ ከእነርሱ ጋር ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊቀ ካህናቱ ሐና፣ ቀያፋ፣ ዮሐንስ፣ እስክንድሮስና የሊቀ ካህናቱ ቤተ ዘመዶች ሁሉ በዚያ ተገኝተው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከተሰበሰቡት ሰዎች መካከል የካህናት አለቃው ሐናና ቀያፋ፥ ዮሐንስና እስክንድሮስ፥ የካህናት አለቃው ቤተሰቦች ሁሉ ይገኙባቸዋል፤ |
በዚያችም ዓመት የካህናት አለቃ የነበረው ስሙ ቀያፋ የተባለው ከእነርሱ አንዱ እንዲህ አላቸው፥ “እናንተስ ምንም አታውቁም።
ይህንም በሰሙ ጊዜ ጥዋት ገስግሠው ወደ ቤተ መቅደስ ገቡና አስተማሩ፤ ሊቀ ካህናቱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ግን ጉባኤውንና ከእስራኤልም ቤት ሽማግሌዎችን ሁሉ ሰበሰቡ፤ ሐዋርያትንም ያመጡአቸው ዘንድ ወደ ወኅኒ ቤት ላኩ።