La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 4:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም አሉ፥ “እነ​ዚ​ህን ሰዎች ምን እና​ድ​ር​ጋ​ቸው? እነሆ፥ በእ​ነ​ርሱ የሚ​ደ​ረ​ገው ተአ​ምር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ዘንድ ታወቀ፤ ግል​ጥም ሆነ፤ ልን​ሰ​ው​ረ​ውም አን​ች​ልም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲህም ተባባሉ፤ “እንግዲህ እነዚህን ሰዎች ምን እናድርጋቸው? በኢየሩሳሌም የሚኖር ሁሉ በእነርሱ እጅ የተደረገውን ድንቅ ታምር ዐውቋል፣ ስለዚህ ይህን ማስተባበል አንችልም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“በእነዚህ ሰዎች ምን እንሥራ? የታወቀ ምልክት በእነርሱ እጅ እንደ ተደረገበኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ ተገልጦአልና፤ እንሸሽገው ዘንድ አንችልም፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“እንግዲህ በእነዚህ ሰዎች ላይ ምን እናድርግ? ይህ ታላቅ ተአምር በእነርሱ እጅ መደረጉ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ታውቆአል፤ ስለዚህ ልንክደው አንችልም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የታወቀ ምልክት በእነርሱ እጅ እንደ ተደረገ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ ተገልጦአልና፥ እንሸሽገው ዘንድ አንችልም፤

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 4:16
10 Referencias Cruzadas  

‘የሚቀጥረን ስለ አጣን ነው፤’ አሉት። እርሱም ‘እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም ትቀበላላችሁ፤’ አላቸው።


በዚያን ጊዜም በርባን የሚባል በጣም የታወቀ እስረኛ ነበራቸው።


በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ነሡ ሊመ​ል​ሱ​ላ​ች​ሁና ሊከ​ራ​ከ​ሯ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ችሉ እኔ አፍ​ንና ጥበ​ብን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።


ስለ​ዚ​ህም ነገር ሕዝቡ ሁሉ ሊቀ​በ​ሉት ወጡ፤ ይህን ተአ​ም​ራት እንደ አደ​ረገ ሰም​ተ​ዋ​ልና።


ነገር ግን ይቃ​ወ​ሙት ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ በጥ​በ​ብና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበ​ርና።