ሐዋርያት ሥራ 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው፤ ያንጊዜም እግሩና ቍርጭምጭምቱ ጸና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀኝ እጁንም ይዞ አስነሣው፤ ወዲያውም እግሩና ቍርጭምጭሚቱ በረታ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው፤ በዚያን ጊዜም እግሩና ቁርጭምጭሚቱ ጸና፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀኝ እጁንም ይዞ አስነሣው፤ ወዲያውኑ እግሩና ቊርጭምጭሚቱ በረታ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው፤ በዚያን ጊዜም እግሩና ቍርጭምጭምቱ ጸና፥ |
ጴጥሮስም፥ “ወርቅና ብር የለኝም፤ ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ፥ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥተህ ሂድ” አለው።
እንዲህም አሉ፥ “እነዚህን ሰዎች ምን እናድርጋቸው? እነሆ፥ በእነርሱ የሚደረገው ተአምር በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ሁሉ ዘንድ ታወቀ፤ ግልጥም ሆነ፤ ልንሰውረውም አንችልም።
ዛሬ ለበሽተኛው በተደረገው ረድኤት ምክንያት በእናንተ ዘንድ እኛ የሚፈረድብን ከሆነ እንግዲያ ይህ ሰው በምን ዳነ?