እነሆ አዝዛለሁ፤ እህልም በመንሽ እንደሚዘራ የእስራኤልን ቤት በአሕዛብ ሁሉ መካከል እዘራለሁ፤ ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።
ሐዋርያት ሥራ 27:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀሩትም በመርከቡ ስብርባሪ ዕንጨትና በሳንቃው ላይ ተሻገሩ፤ ሌሎችም በመርከቡ ገመድ ላይ እየተንጠላጠሉ ተሻገሩ፤ ሁሉም እንዲህ ባለ ሁኔታ በደኅና ወደ ምድር ደረሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተቀሩት ደግሞ በሳንቃዎች ወይም በመርከቡ ስብርባሪ እየተንጠላጠሉ እንዲወጡ አዘዘ። በዚህ መንገድ ሁሉም በደኅና ወደ ምድር ደረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀሩትም እኩሌቶቹ በሳንቃዎች ላይ እኩሌቶቹም በመርከቡ ስባሪ ይወጡ ዘንድ አዘዘ። እንዲሁም ሁሉ በደኅና ወደ ምድር ደረሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀሩት ደግሞ በሳንቃዎችና በመርከቡ ስብርባሪዎች ላይ ሆነው እንዲወጡ አዘዘ፤ በዚህ ሁኔታ ሁሉም በደኅና ወደ ምድር ደረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀሩትም እኵሌቶቹ በሳንቃዎች ላይ እኵሌቶቹም በመርከቡ ስባሪ ይወጡ ዘንድ አዘዘ። እንዲሁም ሁሉ በደኅና ወደ ምድር ደረሱ። |
እነሆ አዝዛለሁ፤ እህልም በመንሽ እንደሚዘራ የእስራኤልን ቤት በአሕዛብ ሁሉ መካከል እዘራለሁ፤ ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘ጳውሎስ ሆይ፥ አትፍራ፤ በቄሣር ፊት ልትቆም ይገባሃል፤ ከአንተም ጋር የሚሄዱትን ሁሉ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለአንተ ሰጥቶሃል።’
ጳውሎስም ይህን ባየ ጊዜ ለመቶ አለቃውና ለወታደሮቹ፥ “እነዚህ ቀዛፊዎች በመርከብ ውስጥ ከሌሉ መዳን አትችሉም” አላቸው።