ብዙዎች አሕዛብ እርሱን ያደንቃሉ፤ ነገሥታትም አፋቸውን ይዘጋሉ፤ ስለ እርሱ ያልተወራላቸው ያውቁታልና፥ ያልሰሙትም ያስተውሉታልና።
ሐዋርያት ሥራ 25:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አግሪጳም ፊስጦስን፥ “እኔም ያን ሰው ልሰማው እወዳለሁ” አለው፤ ፊስጦስም፥ “እንግዲያስ ነገ ትሰማዋለህ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አግሪጳም ፊስጦስን፣ “እኔም እኮ ይህ ሰው ሲናገር መስማት እፈልግ ነበር” አለው። እርሱም፣ “እንግዲያውስ ነገ ትሰማዋለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አግሪጳም ፊስጦስን “ያንንስ ሰው እኔ ዳግም እኮ እሰማው ዘንድ እወድ ነበር፤” አለው። እርሱም “ነገ ትሰማዋለህ፤” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አግሪጳም ፊስጦስን “እኔም ይህ ሰው ሲናገር መስማት እፈልጋለሁ” አለው። ፊስጦስም “ነገ ትሰማዋለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አግሪጳም ፊስጦስን፦ “ያንንስ ሰው እኔ ዳግም እኮ እሰማው ዘንድ እወድ ነበር” አለው። እርሱም፦ “ነገ ትሰማዋለህ” አለው። |
ብዙዎች አሕዛብ እርሱን ያደንቃሉ፤ ነገሥታትም አፋቸውን ይዘጋሉ፤ ስለ እርሱ ያልተወራላቸው ያውቁታልና፥ ያልሰሙትም ያስተውሉታልና።
ከዚህም ሁሉ አስቀድሞ ይይዙአችኋል፤ ወደ አደባባዮችም ይወስዱአችኋል፤ ያሳድዱአችኋል፤ ያስሩአችኋል፤ ስለ ስሜም ወደ ነገሥታትና ወደ መሳፍንት ይወስዱአችኋል።
ጌታችንም እንዲህ አለው፥ “ተነሥና ሂድ፤ በአሕዛብና በነገሥታት፥ በእስራኤል ልጆችም ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ አድርጌዋለሁና።