ሐዋርያት ሥራ 22:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ይመረምሩት ዘንድ የሚሹት ተዉት፤ የሻለቃውም ሮማዊ መሆኑን በዐወቀ ጊዜ“ ለምን አሰርሁት?” ብሎ ፈራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እነዚያ ሊመረምሩት ያሰቡት ሰዎች ወዲያው ከርሱ ሸሹ፤ የጦር አዛዡም የሮም ዜጋ መሆኑን ባወቀ ጊዜ፣ በሰንሰለት አስሮት ስለ ነበር ፈራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ሊመረምሩት ያሰቡት ከእርሱ ወዲያው ተለዩ፤ የሻለቃውም ደግሞ ሮማዊ መሆኑን ባወቀ ጊዜ ፈራ፤ አሳስሮት ነበርና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እነዚያ ሊመረምሩት ተዘጋጅተው የነበሩት ሰዎች ወዲያውኑ ከእርሱ ራቁ፤ አዛዡም የሮም ዜጋ የሆነውን ሰው በሰንሰለት ማሰሩን በተገነዘበ ጊዜ ፈራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም ሊመረምሩት ያሰቡት ከእርሱ ወዲያው ተለዩ፤ የሻለቃውም ደግሞ ሮማዊ መሆኑን ባወቀ ጊዜ ፈራ፥ አሳስሮት ነበርና። |
የሻለቃውም መልሶ፥ “እኔ ይህችን ዜግነት ያገኘኋት ብዙ ገንዘብ ሰጥቼ ነው” አለው፤ ጳውሎስም፥ “እኔማ የተወለድሁ በዚያው ነው” አለው።
ሴቶችም እንደ ትንሣኤ ቀን ተነሥተውላቸው ሙታኖቻቸውን ተቀበሉ፤ ተፈርዶባቸው የሞቱም አሉ፤ የምትበልጠውን ሕይወት ያገኙ ዘንድ ሊድኑ አልወደዱምና።