ሐዋርያት ሥራ 22:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዕብራይስጥ ቋንቋ እንደሚነግራቸው በሰሙም ጊዜ ጸጥ ብለው አዳመጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገር በሰሙ ጊዜ፣ ከፊት ይልቅ ጸጥ አሉ። ጳውሎስም እንዲህ አለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዕብራይስጥም ቋንቋ ሲናገር በሰሙ ጊዜ ከፊት ይልቅ ዝም አሉ። እርሱም እንዲህ አለ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገር በሰሙ ጊዜ በይበልጥ ጸጥ አሉ፤ ጳውሎስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዕብራይስጥም ቋንቋ ሲናገር በሰሙ ጊዜ ከፊት ይልቅ ዝም አሉ። እርሱም አለ፦ |
በፈቀደለትም ጊዜ ጳውሎስ በደረጃው ላይ ቆሞ እጁን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ፤ እጅግም ጸጥታ በሆነ ጊዜ ጳውሎስ በዕብራይስጥ ቋንቋ ተናገረ፤ እንዲህም አለ።