ሐዋርያት ሥራ 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኩሌቶቹ ግን “እነዚህስ ጉሽ ጠጅ ጠግበው ሰክረዋል” ብለው ሳቁባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳንዶቹ ደግሞ “ያልፈላ ብዙ የወይን ጠጅ ጠጥተዋል” በማለት አፌዙባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌሎች ግን እያፌዙባቸው “ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል፤” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዳንዶቹ ግን “አዲስ የወይን ጠጅ ጠጥተው ሰክረዋል!” እያሉ አፌዙባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌሎች ግን እያፌዙባቸው፦ “ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል” አሉ። |
ወደ ዘንባባው ዛፍ እወጣለሁ ጫፉንም እይዛለሁ አልሁ፤ ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ ናቸው፥ የአፍንጫሽም ሽታ እንደ እንኮይ ነው።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ለሕዝቡ ሁሉ ግብዣን ያደርጋል፤ በዚህ ተራራ ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ፤ የወይን ጠጅንም ይጠጣሉ፤ ዘይትንም ይቀባሉ።
የኤፍሬምም ሰዎች እንደ ኃያላን ይሆናሉ፥ ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ደስ ይለዋል፣ ልጆቻቸውም አይተው ደስ ይላቸዋል፥ ልባቸውም በእግዚአብሔር ሐሤት ያደርጋል።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፣ እነርሱም ይበሉአቸዋል፥ የወንጭፉንም ድንጋዮች ይረግጣሉ፣ እንደ ወይን ጠጅም ይጠጡአቸዋል፥ እንደ ጥዋዎችም እንደ መሠዊያም ማዕዘኖች የተሞሉ ይሆናሉ።
ሕዝቡ ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰቡ፥ ሁሉም በልዩ ልዩ ቋንቋ ቢናገሩ፥ አላዋቂዎች፥ ወይም የማያምኑ ቢመጡ አብደዋል ይሉአቸው የለምን?