ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፥ “የምንጠጣውን ውኃ ስጠን” አሉ። ሙሴም፥ “ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው።
ሐዋርያት ሥራ 15:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እግዚአብሔርን አትፈታተኑት፤ እኛም አባቶቻችንም ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ ለምን ትጭናላችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ፣ አባቶቻችንም እኛም ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን ለምን አሁን እግዚአብሔርን ትፈታተኑታላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን እግዚአብሔርን አሁን ስለምን ትፈታተናላችሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ አባቶቻችንም ሆኑ እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በአማኞች ጫንቃ ላይ በመጫን ለምን አሁን እግዚአብሔርን ትፈታተኑታላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን እግዚአብሔርን አሁን ስለ ምን ትፈታተናላችሁ? |
ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፥ “የምንጠጣውን ውኃ ስጠን” አሉ። ሙሴም፥ “ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው።
ጴጥሮስም፥ “እንግዲህ የእግዚአብሔርን መንፈስ ትፈታተኑት ዘንድ እንዴት ተባበራችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግሮች በበር ናቸው፤ አንቺንም ይወስዱሻል” አላት።
ዛሬ ግን እግዚአብሔርን ዐወቃችሁት፤ ይልቁንም እርሱ ዐወቃችሁ፤ እንደ ገና ደግሞ ወደዚያ ወደ ደካማው፥ ወደ ድሀው ወደዚህ ዓለም ጣዖት ተመልሳችሁ፥ ትገዙላቸው ዘንድ እንዴት ፈጠራን ትሻላችሁ?
ነገር ግን ለሚያቀርበው ሰው ግዳጅ መፈጸም የማይቻለውን መባና መሥዋዕት ያቀርቡበት የነበረው ለዚህ ዘመን ምሳሌ ሆነ።