ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም፤ እንዲህም አለው፥ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ትነግሥ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶሃል፤ የእግዚአብሔርንም ሕዝብ ትገዛለህ፤ በዙሪያውም ካሉ ጠላቶቻቸው እጅ ታድናቸዋለህ። እግዚአብሔርም በርስቱ ላይ ትነግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምልክቱ ይህ ነው።
ሐዋርያት ሥራ 13:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ወዲያ ንጉሥ ያነግሥላቸው ዘንድ ለመኑ፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ነገድ የተወለደውን ሰው የቂስን ልጅ ሳኦልን አርባ ዓመት አነገሠላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሕዝቡ ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው ለመኑት፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ወገን፣ የቂስን ልጅ ሳኦልን ሰጣቸው፤ እርሱም አርባ ዓመት ገዛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ወዲያ ንጉሥን ያነግሥላቸው ዘንድ ለመኑ፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ወገን የሚሆን ሰው የቂስን ልጅ ሳኦልን አርባ ዓመት ሰጣቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚያም ቀጥሎ ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው እግዚአብሔርን ለመኑ፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ወገን የሆነውን የቂስን ልጅ ሳኦልን ለአርባ ዓመት አነገሠላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ወዲያ ንጉሥን ያነግሥላቸው ዘንድ ለመኑ፥ እግዚአብሔርም ከብንያም ወገን የሚሆን ሰው የቂስን ልጅ ሳኦልን አርባ ዓመት ሰጣቸው፤ |
ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም፤ እንዲህም አለው፥ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ትነግሥ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶሃል፤ የእግዚአብሔርንም ሕዝብ ትገዛለህ፤ በዙሪያውም ካሉ ጠላቶቻቸው እጅ ታድናቸዋለህ። እግዚአብሔርም በርስቱ ላይ ትነግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምልክቱ ይህ ነው።
ሕዝቡም ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄዱ፤ ሳሙኤልም ሳኦልን ቀብቶ በእግዚአብሔር ፊት በጌልጌላ አነገሠው፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት የእህል ቍርባንና የሰላም መሥዋዕት አቀረበ፤ በዚያም ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ አደረጉ።
ሳሙኤልም ሳኦልን አለው፥ “በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እቀባህ ዘንድ እግዚአብሔር ላከኝ፤ አሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስማ።
እንዲህም አሉት፥ “እነሆ፥ አንተ ሸምግለሃል፤ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም፤ አሁንም እንደ ሌሎች አሕዛብ ሁሉ የሚፈርድልን ንጉሥ አንግሥልን።”
ከብንያም ልጆች ስሙ ቂስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፥ እርሱም የአብሔል ልጅ፥ የያሬድ ልጅ፥ የባሔር ልጅ፥ የብንያም ሰው፥ የአፌቅ ልጅ፥ ጽኑዕ ኀያል ሰው ነበረ።