La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 11:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያ​ችም ሰዓት ከቂ​ሳ​ርያ ወደ እኔ የተ​ላኩ ሦስት ሰዎች መጡ፤ እኔ ባለ​ሁ​በት ግቢ በርም ቆሙ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ልክ በዚያው ሰዓት፣ ሦስት ሰዎች ከቂሳርያ ወደ እኔ ተልከው መጥተው እኔ ባለሁበት ቤት ደጅ ላይ ቆሙ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆም፥ ያንጊዜ ሦስት ሰዎች ከቂሣርያ ወደ እኔ ተልከው ወዳለሁበት ቤት ቀረቡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነሆ፥ በዚያን ጊዜ ከቂሳርያ ወደ እኔ የተላኩ ሦስት ሰዎች እኔ ወደነበርኩበት ቤት ደረሱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆም፥ ያን ጊዜ ሦስት ሰዎች ከቂሣርያ ወደ እኔ ተልከው ወዳለሁበት ቤት ቀረቡ።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 11:11
7 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ሌዋ​ዊው ወን​ድ​ምህ አሮን አለ አይ​ደ​ለ​ምን? እርሱ እን​ደ​ሚ​ና​ገ​ር​ልህ አው​ቃ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ እርሱ ሊገ​ና​ኝህ ይመ​ጣል፤ በአ​የ​ህም ጊዜ በልቡ ደስ ይለ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን አለው፥ “ሄደህ በም​ድረ በዳ ሙሴን ተገ​ና​ኘው፤” ሄዶም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ተገ​ና​ኘው፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተሳ​ሳሙ።


ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?” ብሎ ጠየቀ።


እን​ዲ​ህም መላ​ልሶ ሦስት ጊዜ ነገ​ረኝ፤ ዳግ​መ​ኛም ሁሉ ተጠ​ቅ​ልሎ ወደ ሰማይ ተመ​ለሰ።


ፊል​ጶ​ስም አዛ​ጦን ወደ​ም​ት​ባል ሀገር ደረሰ፤ በከ​ተ​ማ​ዎ​ችም ሁሉ እየ​ተ​ዘ​ዋ​ወረ ወደ ቂሳ​ርያ እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ ያስ​ተ​ምር ነበር።