የተማሩትንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አልጠበቁም። ነገር ግን ለጣዖት መስገድን፥ የሚገባ ያይደለ የጐደፈ ሥራንም ሁሉ፥ በኮከብ ማሟረትን፥ ጥንቆላንና ጣዖት ማምለክን፥ ክፉ ፈቃድንና እግዚአብሔር የማይወድደውንም ሥራ ሁሉ ተማሩ።