የምትሞቱበትን ቀን አስቡ፤ ነፍሳችሁ ከሥጋችሁ በምትለይበት ጊዜ፥ ገንዘባችሁንም ለሌላ በምትተዉበት ጊዜ፥ ወደማታውቁትም መንገድ በምትሄዱበት ጊዜ የምትመጣባችሁን አስቧት።