Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽ​ሐፈ መቃ​ብ​ያን ሣልስ 6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የም​ት​ሞ​ቱ​በ​ትን ቀን አስቡ፤ ነፍ​ሳ​ችሁ ከሥ​ጋ​ችሁ በም​ት​ለ​ይ​በት ጊዜ፥ ገን​ዘ​ባ​ች​ሁ​ንም ለሌላ በም​ት​ተ​ዉ​በት ጊዜ፥ ወደ​ማ​ታ​ው​ቁ​ትም መን​ገድ በም​ት​ሄ​ዱ​በት ጊዜ የም​ት​መ​ጣ​ባ​ች​ሁን አስ​ቧት።

2 የሚ​ቀ​በ​ሏ​ች​ሁም ክፉ​ዎች ናቸው፤ በመ​ል​ካ​ቸ​ውም ጥፉ​ዎች ናቸው፤ በግ​ር​ማ​ቸ​ውም የሚ​ያ​ስ​ፈሩ ናቸው፤ ቃላ​ች​ሁን አይ​ሰ​ሙም፤ ቃላ​ቸ​ው​ንም አት​ሰ​ሙም።

3 የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ፈቃድ ስለ አላ​ደ​ረ​ጋ​ችሁ በለ​መ​ና​ች​ኋ​ቸው ጊዜ አይ​መ​ል​ሱ​ላ​ች​ሁም፤ ስለ​ዚ​ህም እጅግ ያስ​ፈ​ሯ​ች​ኋል።

4 አጋ​ን​ንት ይፈ​ሯ​ቸ​ዋ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ በሚ​ፈ​ጽሙ ሰዎች ግን ፍር​ሀት የለ​ባ​ቸ​ውም። በኃ​ጥ​ኣን ነፍ​ሳ​ትም አጋ​ን​ንት ይዘ​ባ​በ​ቱ​ባ​ቸ​ዋል።

5 ይህን ዓለም ስለ ናቁት እጅግ ደስ ያሰ​ኛ​ቸ​ዋ​ልና የጻ​ድ​ቃን ሰዎች ነፍ​ሳት በመ​ላ​እ​ክት ይባቤ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ የኃ​ጥ​ኣን ነፍ​ሳ​ትን ግን ክፉ​ዎች መላ​እ​ክት ይቀ​በ​ሏ​ቸ​ዋል።

6 የጻ​ድ​ቃ​ንን ነፍ​ሳት ያረ​ጋ​ጓ​ቸው ዘንድ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይላ​ካ​ሉና፥ የጻ​ድ​ቃ​ን​ንና የደ​ጋ​ጎች ነፍ​ሳ​ትን የም​ሕ​ረት መላ​እ​ክት ይቀ​በ​ሉ​አ​ቸ​ዋል። የኃ​ጥ​ኣ​ንን ነፍ​ሳት ግን ክፉ​ዎች አጋ​ን​ንት ይቀ​በ​ሏ​ቸ​ዋል፤ በኃ​ጥ​ኣን ነፍ​ሳት ይዘ​ባ​በ​ቱ​ባ​ቸው ዘንድ ከዲ​ያ​ብ​ሎስ ይላ​ካ​ሉና።

7 ኃጥ​ኣን ወዮ​ላ​ችሁ፤ የም​ት​ሞ​ቱ​ባት ቀን ሳት​ደ​ር​ስ​ባ​ችሁ ለራ​ሳ​ችሁ አል​ቅሱ፤ ከሞ​ታ​ችሁ በኋላ ያለ​ፈው ዘመ​ና​ችሁ አይ​መ​ለ​ስም።

8 ነገር ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በደ​ረ​ሳ​ችሁ ጊዜ ያለ መከ​ራና ያለ ደዌ በደ​ስታ ትኖሩ ዘንድ ዘመ​ና​ችሁ ሳያ​ልፍ በአ​ላ​ች​ሁ​በት ንስሓ ግቡ።

9 ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ያ​ርቅ ከንቱ ፈቃድ እን​ዳ​ይ​ስ​ባ​ችሁ፥ በእ​ና​ንተ ጽኑ ነቀ​ፋና መቀ​ማ​ጠል፥ መብ​ል​ንና ደስ​ታ​ንም መው​ደድ አይ​ገ​ኝ​ባ​ችሁ፤ ያለ ልክ የጠ​ገ​በች ሰው​ነት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም አታ​ስ​ብ​ምና የዲ​ያ​ብ​ሎስ መን​ፈስ ያድ​ር​ባ​ታል እንጂ በእ​ር​ስዋ የሕ​ይ​ወት መን​ፈስ አያ​ድ​ር​ባ​ትም።

10 ሙሴ፥ “ያዕ​ቆብ በልቶ ጠገበ ወፈ​ረም፥ ሰባ፥ ሰፋም፥ የፈ​ጠ​ረው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተወው፤

11 ሕይ​ወ​ቱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራቀ” ብሎ እንደ ተና​ገረ፥ ያለ ልክ የሆድ ጥጋብ እን​ዳ​ለሌ ፈረስ መሆን ነውና፥ ያለ ልክ መብ​ላ​ትና መጠ​ጣት፥ ማመ​ን​ዘ​ርም እንደ ምድረ በዳ እሪያ መሆን ነውና።

12 በልክ የሚ​በላ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ረት የጸና ይሆ​ናል፤ እንደ አድ​ማ​ስም ድን​ጋይ፥ አጥ​ርም እን​ዳ​ለው ግንብ ይጸ​ናል። “ኀጢ​አ​ተኛ የሚ​ያ​ባ​ር​ረው ሳይ​ኖር ይሸ​ሻል” ተብ​ሎ​አ​ልና።

13 ጻድቅ ግን እንደ አን​በሳ ተዘ​ልሎ ይኖ​ራል።

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የማ​ይ​ወዱ ሰዎች ግን ቃሉን አይ​ጠ​ብ​ቁም፤ ልቡ​ና​ቸ​ውም የቀና አይ​ደ​ለም።

15 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ሳሉ እን​ዳ​ያ​ርፉ በመ​ን​ቀ​ጥ​ቀ​ጥና በፍ​ር​ሀት፥ ገን​ዘ​ባ​ቸ​ው​ንም በመ​ን​ጠቅ፥ ቍጥ​ርም በሌ​ለው ብዙ መከራ ተይ​ዘው ከጌ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ እጃ​ቸ​ውን በሰ​ን​ሰ​ለት ታስ​ረው፥

16 ከመ​ከ​ራ​ውም ያረፉ እን​ዳ​ይ​ሆኑ፥ አኗ​ኗ​ራ​ቸ​ውም በሰ​ላም እን​ዳ​ይ​ሆን በተ​ለ​ያዩ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግጡ መከ​ራ​ዎች ሳሉ ኀዘ​ን​ንና ድን​ጋ​ጤን ያመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋል።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos