እርሱም አላቸው፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን፥ አትፍሩ፤ አምላካችሁ የአባቶቻችሁ አምላክ በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ፤ ብራችሁንስ መዝኜ ተቀብያለሁ።”
3 ዮሐንስ 1:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ወዲያው ላይህ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አፍ ለአፍም እንነጋገራለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቅርቡ ላይህ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ፊት ለፊትም እንነጋገራለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ወዲያው ላይህ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ፊት ለፊት እንነጋገራለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቅርቡ ላይህ ተስፋ አደርጋለሁ፤ በዚያን ጊዜ ቃል በቃል እንነጋገራለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ወዲያው ላይህ ተስፋ አደርጋለሁ፥ አፍ ለአፍም እንነጋገራለን። |
እርሱም አላቸው፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን፥ አትፍሩ፤ አምላካችሁ የአባቶቻችሁ አምላክ በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ፤ ብራችሁንስ መዝኜ ተቀብያለሁ።”
ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ቃሉን ይሰሙታል፤ እርሱም በጎቹን በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ አውጥቶም ያሰማራቸዋል።
ያም ከሳምንቱ የመጀመሪያው ቀን በመሸ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን ስለ ፈሩ ተሰብስበው የነበሩበት ቤት ደጁ ተቈልፎ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ መጥቶ በመካከላቸው ቆመና፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው።
ጌታችን ኢየሱስም ዳግመኛ እንዲህ አላቸው፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አብ እኔን እንደ ላከኝ እንዲሁ እኔ እናንተን እልካችኋለሁ።”
ከአባታችን ከእግዚአብሔር አብ፥ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስም ከእምነት ጋር ሰላምና ፍቅር ለወንድሞቻችን ይሁን።
እንድጽፍላችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር ሳለኝ በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልወድም፤ ዳሩ ግን ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ ልመጣ አፍ ለአፍም ልናገራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።