በጦር ወድቀዋልና ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን፥ ለይሁዳም ሕዝብ ለእስራኤልም ወገን እንባ እያፈሰሱ አለቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ።
2 ሳሙኤል 3:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጆችህ አልታሰሩም፤ እግሮችህም በሰንሰለት አልተያዙም፤ ማንም እንደ ሰነፍ አልወሰደህም፤ በዐመፃ ልጆችም ፊት ወደቅህ።” ሕዝቡም ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እጆችህ አልታሰሩም፤ እግሮችህ በእግር ብረት አልገቡም፤ ሰው በክፉ ሰዎች ፊት እንደሚወድቅ አንተም እንደዚሁ ወደቅህ።” ሕዝቡም ሁሉ እንደ ገና አለቀሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አበኔር እንደ ተራ ሰው ይሙት? እግሮችህ በእግር ብረት አልገቡም፤ ሰው በክፉ ሰዎች ፊት እንደሚወድቅ አንተም እንደዚሁ ወደቅህ።” ሕዝቡም ሁሉ እንደገና አለቀሱለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጆችህ አልታሰሩም፤ እግሮችህ አልታበቱም፤ ታዲያ፥ በዚህ ሁኔታ ሳለ በወንጀለኞች እጅ እንደሚወድቅ ሰው እንዴት ተገደልክ!” ሕዝቡም ሁሉ ስለ እርሱ እንደገና አለቀሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጅህ አልታሰረም፥ እግርህም በሰንሰለት አልተያዘም፥ ሰው በዓመፀኞች ፊት እንደሚወድቅ አንተ እንዲሁ ወደቅህ ብሎ የልቅሶ ቅኔ ተቀኘለት። ሕዝቡም ሁሉ ዋይታ አብዝተው አለቀሱ። |
በጦር ወድቀዋልና ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን፥ ለይሁዳም ሕዝብ ለእስራኤልም ወገን እንባ እያፈሰሱ አለቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ።
ሕዝቡም ሁሉ ገና ሳይመሽ ዳዊትን እንጀራ ይበላ ዘንድ ሊጋብዙት መጡ፤ ዳዊት ግን፥ “ፀሐይ ሳትጠልቅ እንጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀምስ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፥ ይህንም ይጨምርብኝ” ብሎ ማለ።
ይኸውም ሙሾ ነው፤ ሙሾን ያሞሹለታል፤ የአሕዛብ ሴቶች ልጆች ያሞሹለታል፤ ስለ ግብፅና ስለ ኀይልዋ ሁሉ ያሞሹለታል፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ሰውን እንደሚያደቡ ወንበዴዎች፥ እንዲሁ ካህናት በሴኬም መንገድ ላይ አድብተው ይገድላሉ፤ ዐመፅንም ያደርጋሉ።
ፍልስጥኤማውያንም ይዘው ዐይኖቹን አወጡት፤ ወደ ጋዛም አውርደው በእግር ብረት አሰሩት፤ በግዞትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር።