አቤሴሎምም፥ “አንተ እንቢ ካልህ ወንድሜ አምኖን ከእኛ ጋር እንዲሄድ እለምንሃለሁ” አለ። ንጉሡም፥ “ከአንተ ጋር ለምን ይሄዳል?” አለው።
2 ሳሙኤል 3:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቈይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፤ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ወገቡን መታው፤ ሞተም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አበኔር ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፣ ኢዮአብ በቈይታ የሚያነጋግረው በመምሰል ዞር አድርጎ ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሲል፣ ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፥ ኢዮአብ ለብቻው የሚያነጋግረው በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አበኔር ወደ ኬብሮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብ በግል ሊያነጋግረው የፈለገ በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ገለል አድርጎ ወሰደው፤ እዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ ኢዮአብ ይህን ያደረገበት ምክንያት አበኔር ቀደም ብሎ ወንድሙን ዐሣሄልን ስለ ገደለበት ለመበቀል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቆይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፥ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ሆዱን መታው፥ ሞተም። |
አቤሴሎምም፥ “አንተ እንቢ ካልህ ወንድሜ አምኖን ከእኛ ጋር እንዲሄድ እለምንሃለሁ” አለ። ንጉሡም፥ “ከአንተ ጋር ለምን ይሄዳል?” አለው።
ለአሚሳይም፦ አንተ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቍራጭ አይደለህምን? በዘመንህም ሁሉ በኢዮአብ ፋንታ በፊቴ የሠራዊት አለቃ ሳትሆን ብትቀር ዛሬ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ይህንም ይጨምርብኝ በሉት።”
ኢዮአብም ከዳዊት በወጣ ጊዜ መልእክተኞችን ከአበኔር በኋላ ላከ፤ ከሴይርም ጕድጓድ መለሱት። ዳዊት ግን ይህን አላወቀም።
ከዚህም በኋላ ዳዊት ሰማ፤ እንዲህም አለ፥ “ከኔር ልጅ ከአበኔር ደም በእግዚአብሔር ዘንድ ለዘለዓለም እኔ ንጹሕ ነኝ፤ መንግሥቴም ንጹሕ ነው፤
አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ከእርሱ የሚሻሉትን ሁለቱን ጻድቃን ሰዎች፥ የእስራኤልን ሠራዊት አለቃ የኔርን ልጅ አበኔርን፥ የይሁዳንም ሠራዊት አለቃ የኢያቴርን ልጅ አሜሳይን በሰይፍ ገድሎአልና እግዚአብሔር የዐመፅ ደሙን በራሱ ላይ መለሰ።
አንተም ደግሞ የሶርህያ ልጅ ኢዮአብ፥ ሁለቱን የእስራኤል ሠራዊት አለቆች የኔር ልጅ አበኔርን የኢያቴርንም ልጅ አሜሳይን ገድሎ፥ በእኔ ላይ ያደረገውን ታውቃለህ፤ የጦርነትንም ደም በሰላም አፈሰሰ፤ በወገቡም ባለው ድግና በእግሩም ባለው ጫማ ንጹሕ ደም አኖረ።
በገለዓድ ምድር ባለው በምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ የዘብድያስ ልጅ ኢዮዳኢ፤ በብንያምም ልጆች ላይ የአበኔር ልጅ አሳሄል፤
የናታንያም ልጅ እስማኤል ከእርሱም ጋር የነበሩት ዐሥሩ ሰዎች ተነሥተው የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መቱ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በሀገሩ ላይ የሾመውን ገደሉ።