La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 3:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አበ​ኔ​ርም ዳዊ​ትን፥ “ተነ​ሥቼ ልሂድ፤ ካንተ ጋርም ቃል ኪዳን እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ ነፍ​ስ​ህም እንደ ወደ​ደች ሁሉን እን​ድ​ት​ገዛ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ለጌ​ታዬ ለን​ጉሥ ልሰ​ብ​ስብ” አለው። ዳዊ​ትም አበ​ኔ​ርን አሰ​ና​በ​ተው፤ በሰ​ላ​ምም ሄደ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም አበኔር ዳዊትን፤ “ከአንተ ጋራ ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ፣ ልብህ እንደተመኘውም ሁሉን እንድትገዛ ፈጥኜ ሄጄ፣ ለጌታዬ ለንጉሡ መላውን እስራኤልን ልሰብስብ” አለው። ስለዚህ ዳዊት አበኔርን አሰናበተው፤ በሰላምም ሄደ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም አበኔር ዳዊትን፥ “ለጌታዬ ለንጉሡ መላውን እስራኤልን ልሰብስብ፥ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ፥ ልብህ እንደተመኘውም ሁሉን እንድትገዛ ፈጥኜ ልሂድ” አለው። ስለዚህ ዳዊት አበኔርን አሰናበተው፤ በሰላምም ሄደ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አበኔርም ዳዊትን “ከአንተ ጋር እንዲነጋገሩና እንዲዋዋሉ አንተም ልብህ በተመኘው ሁሉ ላይ እንድትነግሥ ለማድረግ ወደ እስራኤላውያን ልሂድ” አለው። በዚህም ዐይነት ዳዊት አበኔርን በሰላም አሰናበተው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አበኔርም ዳዊትን፦ ተነሥቼ ልሂድ፥ ከአንተ ጋርም ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ፥ ነፍስህም እንደ ወደደች ሁሉን እንድትገዛ እስራኤልን ሁሉ ለጌታዬ ለንጉሥ ልሰብስብ አለው። ዳዊትም አበኔርን አሰናበተው፥ በደኅናም ሄደ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 3:21
8 Referencias Cruzadas  

በገ​ለ​ዓ​ድና በታ​ሲሪ፥ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ልም፥ በኤ​ፍ​ሬ​ምም፥ በብ​ን​ያ​ምም፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ላይ አነ​ገ​ሠው።


የዳ​ዊ​ት​ንም ዙፋን በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ መን​ግ​ሥ​ትን ከሳ​ኦል ቤት ወሰ​ዳት።”


አበ​ኔ​ርም ለዳ​ዊት፥ “ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርግ፤ እጄም ከአ​ንተ ጋር ትሆ​ና​ለች፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ ወደ አንተ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ” ብለው በስሙ ይነ​ግ​ሩት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ወዲ​ያ​ውኑ ላከ​ለት።


አበ​ኔ​ርም ከሃያ ሰዎች ጋር ወደ ዳዊት ወደ ኬብ​ሮን መጣ፤ ዳዊ​ትም ለአ​በ​ኔ​ርና ከእ​ርሱ ጋር ለነ​በ​ሩት ሰዎች ግብዣ አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብ​ሮን መጡ፤ ንጉሡ ዳዊ​ትም በኬ​ብ​ሮን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊ​ትን ቀቡት።


አን​ተ​ንም እወ​ስ​ድ​ሃ​ለሁ፤ ነፍ​ስ​ህም በወ​ደ​ደ​ችው ሁሉ ላይ አነ​ግ​ሥ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ንጉሥ ትሆ​ና​ለህ።


ሕይ​ወ​ትን ለመ​ነህ፥ ሰጠ​ኸ​ውም፥ ለረ​ዥም ዘመን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ።


የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ያይ​ደለ፥ ሁሉም የራ​ሱን ጉዳይ ያስ​ባ​ልና።