2 ሳሙኤል 24:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ገለዓድም አዳሳይ ወደምትባል ወደ ተባሶን ሀገርም መጡ፤ ወደ ዳኒዳንና ወደ ኡዳንም ደረሱ፤ ወደ ሲዶናም ዞሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ወደ ገለዓድና ወደ ተባሶን አዳሰይ፣ ቀጥሎም ወደ ዳንየዓን ከዚያም ዞረው ወደ ሲዶና ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ወደ ገለዓድና በሒታውያን ግዛት ወዳለው ወደ ቃዴስ ዘለቁ፤ ከዚያም ወደ ዳን፥ ከዳንም ወደ ሲዶና ዞሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥለውም ወደ ገለዓድና በሒታውያን ግዛት ውስጥ ወዳለው ወደ ቃዴስ ዘለቁ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ዳን፥ ከዳንም ወደ ምዕራብ ታጥፈው ወደ ሲዶና ሄዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ገለዓድም ወደ ተባሶን አዳሰይ አገር መጡ፥ ወደ ዳንየዓንም ደረሱ፥ ወደ ሲዶናም ዞሩ፥ |
ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች እጅግ ብዙ እንስሶች ነበሩአቸው፤ እነሆም፥ የኢያዜር ምድርና የገለዓድ ምድር የከብት ሀገር እንደ ነበረ አዩ።
እግዚአብሔርም በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ መቱአቸውም፤ ወደ ታላቂቱም ሲዶና፥ ወደ ማሴሮንም፥ በምሥራቅም በኩል ወዳለው ወደ ሞሳሕ ሸለቆ አሳደዱአቸው፤ ማንንም ሳያስቀሩ መቱአቸው።
የዳን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። የዳን ልጆችም በተራራው ላይ የሚያስጨንቋቸው አሞሬዎናውያንን አላስጨነቁአቸውም። አሞሬዎናውያንም ወደ ሸለቆዎች ይወርዱ ዘንድ አልፈቀዱላቸውም። ከእነርሱም ከርስታቸው ዳርቻ አንድ ክፍልን ወሰዱ።
አሴርም የዓኮ ነዋሪዎችን አላጠፋቸውም፤ ነገር ግን ገባሮች ሆኑላቸው፤ የዶር ነዋሪዎችንና የሲዶን ነዋሪዎችን፥ የደላፍንም ነዋሪዎች፥ የአክሶዚብንና የሄልባን፥ የአፌቅንና የረዓብንም ሰዎች አላጠፉአቸውም።