2 ሳሙኤል 23:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳዊት ኀያላን ስም ይህ ነው። የሦስተኛው ክፍል አለቃ የሆነ ከነዓናዊው ኢያቡስቴ ነበረ፤ ጎራዴውን መዝዞ ስምንት መቶ ያህል ጭፍሮችን በአንድ ጊዜ የገደለ አሶናዊው አዲኖን ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም ይህ ነው፤ የታሕክሞን ሰው ዮሴብ በሴትቤት የሦስቱ አለቆች አለቃ ሲሆን፣ እርሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰው የገደለ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም የሚከተለው ነው፤ የታሕክሞን ሰው ዮሼብ ባሼቤት የሦስቱ አለቆች አለቃ ሲሆን፥ እርሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰው በአንዴ የገደለ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዝነኞች የሆኑት የዳዊት ወታደሮች ስም ዝርዝር ከዚህ በታች እንደ ተመለከተው ነው፤ የመጀመሪያው የታሕክሞን ተወላጅ ዮሼብ ባሼቤት የተባለው ሲሆን እርሱም ከሦስቱ ኀያላን ብልጫ ያለው ተቀዳሚ ነው፤ ይህ ሰው በአንድ ውጊያ ላይ ጦሩን አንሥቶ ስምንት መቶ ኀያላን ሰዎችን ገደለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊት ኃያላን ስም ይህ ነው። የአለቆች አለቃ የሆነ ከነዓናዊው ኢያቡስቴ ነበረ፥ እርሱም ጦሩን አንሥቶ ስምንት መቶ ያህል በአንድ ጊዜ ገደለ። |
ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅና የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነቢዩም ናታን፥ ሳሚም፥ ሬሲም፥ የዳዊትም ኀያላን አዶንያስን አልተከተሉም ነበር።
ለዳዊትም የነበሩት ኀያላን አለቆች እነዚህ ናቸው፤ ስለ እስራኤል እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ያነግሡት ዘንድ ከእስራኤል ሁሉ ጋር በመንግሥቱ አጸኑት።
የእስራኤልም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆችና የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆችም ለንጉሡና ለንጉሡ ትእዛዝ ሁሉ የሚያገለግሉ ሹማምት እንደ ቍጥራቸው በየክፍላቸው እነዚህ ነበሩ። እነዚህም ክፍሎች እያንዳንዳቸው ሃያ አራት ሺህ ሆነው በዓመቱ ወራት ሁሉ በየወሩ ይገቡና ይወጡ ነበር።
ለመጀመሪያው ወር በአንደኛው ክፍል ላይ የዘብድኤል ልጅ ያሶብአም ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
አስተዋይና ጸሓፊ የነበረው በአባቱ በኩል የዳዊት አጎት ዮናታን አማካሪ ነበረ፤ የአክማኔም ልጅ ኢያሔኤል ከንጉሡ ልጆች ጋር ነበረ፤