2 ሳሙኤል 23:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ብርሃን በጥዋት፥ በማለዳም ፀሐይ ይወጣል፤ ብርሃኑም በነግህ ይመጣል፤ ከዝናምም የተነሣ በምድር ሐመልማል ይለመልማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ፣ ደመና በሌለበት፣ በማለዳ ፀሓይ በምትወጣበት ጊዜ፣ እንዳለው ብርሃን ነው፤ በምድር ላይ ሣርን እንደሚያበቅለው፣ ከዝናብም በኋላ እንዳለው የብርሃን ጸዳል ነው።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ፥ እንደ ንጋት ብርሃን እንደ ማለዳ ፀሐይ አወጣጥ፥ ደመና በሌለበት ማለዳ እንደምታበራ የብርሃን ጸዳል፥ ከዝናብ በኋላ ከምድር እንደሚበቅል ልምላሜ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዝናብ በኋላ ደመና እንደሌለው ንጋት፥ ምድርንም ሣር እንድታበቅል እንደሚያደርግ፥ እንደ ንጋት የፀሐይ ብርሃን ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ እንደ ማለዳ ብርሃን እንደ ፀሐይ አወጣጥ፥ በጥዋትም ያለ ደመና እንደሚደምቅ፥ ከዝናብ በኋላ ከምድር እንደሚበቅል ልምላሜ ይሆናል። |
በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከእስራኤል የተረፉትን ያከብርና ከፍ ያደርግ ዘንድ በጌትነቱ ምክር በምድር ላይ ያበራል።
እንወቀው፤ እናውቀውም ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል፤ እንደ ወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን፤ በምድርም ላይ እንደ መጀመሪያውና እንደ ኋለኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።
የያዕቆብም ቅሬታ በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውንም እንደማይጠብቅ፥ የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ይሆናል።
ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፣ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።
ትምህርቴንም እንደ ዝናም ተስፋ ታድርገው፤ ነገሬ እንደ ጠል ይውረድ፤ በእርሻም ላይ እንደ ዝናም፥ በሣርም ላይ እንደ ጤዛ።
አቤቱ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ፤ ወዳጆችህ ግን ፀሐይ በኀይሉ በወጣ ጊዜ እንደሚሆን፤ እንዲሁ ይሁኑ። ምድሪቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረፈች።