La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 23:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የዳ​ዊት ኀያ​ላ​ንም ስማ​ቸው ይህ ነው። የኢ​ዮ​አብ ወን​ድም አሣ​ሄል በሠ​ላ​ሳው መካ​ከል ነበረ፤ የቤተ ልሔም ሰው የአ​ጎቱ የዱዲ ልጅ ኤል​ያ​ናን፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከሠላሳዎቹ መካከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፤ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣ የቤተ ልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከሠላሳዎቹ መካከል፦ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፥ የቤተልሔሙ ሰው የዶዶ ልጅ ኤልሐናን፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከሠላሳዎቹ መካከል የሌሎቹ ሰዎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የኢዮአብ ወንድም ዐሣሄል፤ የቤተልሔሙ ተወላጅ የዶዶ ልጅ ኤልሐናን፤ የሐሮድ ተወላጆች የሆኑት ሻማና ኤሊቃ፤ የፌሌጥ ተወላጅ የሆነው ሔሌጽ፤ የተቆዓ ተወላጅ የሆነው የዒቄሽ ልጅ ዒራ፤ የዐናቶት ተወላጅ የሆነው አቢዔዜር፤ የሑሻ ተወላጅ የሆነው መቡናይ፤ የአሖሕ ተወላጅ የሆነው ጻልሞን፤ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው ማህራይ፤ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው የባዕና ልጅ ሔሌብ፤ በብንያም ግዛት የምትገኘው የጊብዓ ተወላጅ የሆነው የሪባይ ልጅ ኢታይ፤ የፒርዓቶን ተወላጅ የሆነው በናያ፤ በጋዓሽ ሸለቆ አጠገብ የተወለደው ሂዳይ፤ የዓርባ ተወላጅ የሆነው ኢቢዓልቦን፤ የባርሑም ተወላጅ የሆነው ዓዝማዌት፤ የሻዓልቦን ተወላጅ የሆነው ኤልያሕባ፤ የያሼን ልጆች፤ ዮናትን፤ የሐራር ተወላጅ የሆነው ሻማ፤ የሐራር ተወላጅ የሆነው የሻራር ልጅ አሒአም፤ የማዕካ ተወላጅ የሆነው የአሐሰባይ ልጅ ኤሊፌሌጥ፤ የጊሎ ተወላጅ የሆነው የአኪጦፌል ልጅ ኤሊዓም፤ የቀርሜሎስ ተወላጅ የሆነው ሔጽሮ፤ የዐረብ ተወላጅ የሆነው ፓዓራይ፤ የጾባ ልጅ የሆነው የናታን ልጅ ዪግአል የጋድ ተወላጅ የሆነው ባኒ፤ የዐሞን ተወላጅ የሆነው ጼሌቅ፤ የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬ የነበረውና የበኤሮት ተወላጅ የሆነው ናሕራይ፤ የያቲር ተወላጆች የሆኑት ዒራና ጋሬብ፤ ሒታዊው ኦርዮን። ዝነኞች የሆኑት ኀያላን ወታደሮች ጠቅላላ ድምር ሠላሳ ሰባት ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የኢዮአብም ወንድም አሣሄል በሠላሳው መካከል ነበረ፥ የቤተ ልሔም ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፥

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 23:24
6 Referencias Cruzadas  

የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብና የዳ​ዊት ብላ​ቴ​ኖች ከኬ​ብ​ሮን ወጥ​ተው በገ​ባ​ዖን ውኃ መቆ​ሚያ አጠ​ገብ ተገ​ና​ኙ​አ​ቸው፤ በው​ኃ​ውም መቆ​ሚያ በአ​ንዱ ወገን እነ​ዚህ፥ በሌ​ላ​ውም ወገን እነ​ዚያ ሆነው ተቀ​መጡ።


በዚ​ያም ሦስቱ የሦ​ር​ህያ ልጆች ኢዮ​አ​ብና አቢሳ፥ አሣ​ሄ​ልም ነበሩ፤ የአ​ሣ​ሄ​ልም እግ​ሮቹ ፈጣ​ኖች ነበሩ፤ እንደ ዱር ሚዳ​ቋም ሯጭ ነበረ።


ደግ​ሞም በሮም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጦር​ነት ሆነ፤ የቤ​ተ​ል​ሔ​ማ​ዊ​ውም የዓ​ሬ​ኦ​ር​ጌም ልጅ ኤል​ያ​ናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠ​ቅ​ለያ የነ​በ​ረ​ውን የጌት ሰው ጎዶ​ል​ያን ገደ​ለው።


ከሦ​ስ​ቱም ይልቅ የከ​በረ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ ሦስቱ አል​ደ​ረ​ሰም። ዳዊ​ትም ትእ​ዛዝ አስ​ከ​ባሪ አድ​ርጎ ሾመው።


ደግ​ሞም በጭ​ፍ​ሮቹ ዘንድ የነ​በ​ሩት ኀያ​ላን እነ​ዚህ ናቸው፤ የኢ​ዮ​አብ ወን​ድም አሣ​ሄል፥ የቤተ ልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤል​ያ​ናን፤


በአ​ራ​ተ​ኛው ወር አራ​ተ​ኛው አለቃ የኢ​ዮ​አብ ወን​ድም አሳ​ሄል ነበረ፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ ልጁ ዝባ​ድ​ያና ወን​ድ​ሞቹ ነበሩ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።