Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 23:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ከሠላሳዎቹ መካከል፦ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፥ የቤተልሔሙ ሰው የዶዶ ልጅ ኤልሐናን፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ከሠላሳዎቹ መካከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፤ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣ የቤተ ልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24-39 ከሠላሳዎቹ መካከል የሌሎቹ ሰዎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የኢዮአብ ወንድም ዐሣሄል፤ የቤተልሔሙ ተወላጅ የዶዶ ልጅ ኤልሐናን፤ የሐሮድ ተወላጆች የሆኑት ሻማና ኤሊቃ፤ የፌሌጥ ተወላጅ የሆነው ሔሌጽ፤ የተቆዓ ተወላጅ የሆነው የዒቄሽ ልጅ ዒራ፤ የዐናቶት ተወላጅ የሆነው አቢዔዜር፤ የሑሻ ተወላጅ የሆነው መቡናይ፤ የአሖሕ ተወላጅ የሆነው ጻልሞን፤ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው ማህራይ፤ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው የባዕና ልጅ ሔሌብ፤ በብንያም ግዛት የምትገኘው የጊብዓ ተወላጅ የሆነው የሪባይ ልጅ ኢታይ፤ የፒርዓቶን ተወላጅ የሆነው በናያ፤ በጋዓሽ ሸለቆ አጠገብ የተወለደው ሂዳይ፤ የዓርባ ተወላጅ የሆነው ኢቢዓልቦን፤ የባርሑም ተወላጅ የሆነው ዓዝማዌት፤ የሻዓልቦን ተወላጅ የሆነው ኤልያሕባ፤ የያሼን ልጆች፤ ዮናትን፤ የሐራር ተወላጅ የሆነው ሻማ፤ የሐራር ተወላጅ የሆነው የሻራር ልጅ አሒአም፤ የማዕካ ተወላጅ የሆነው የአሐሰባይ ልጅ ኤሊፌሌጥ፤ የጊሎ ተወላጅ የሆነው የአኪጦፌል ልጅ ኤሊዓም፤ የቀርሜሎስ ተወላጅ የሆነው ሔጽሮ፤ የዐረብ ተወላጅ የሆነው ፓዓራይ፤ የጾባ ልጅ የሆነው የናታን ልጅ ዪግአል የጋድ ተወላጅ የሆነው ባኒ፤ የዐሞን ተወላጅ የሆነው ጼሌቅ፤ የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬ የነበረውና የበኤሮት ተወላጅ የሆነው ናሕራይ፤ የያቲር ተወላጆች የሆኑት ዒራና ጋሬብ፤ ሒታዊው ኦርዮን። ዝነኞች የሆኑት ኀያላን ወታደሮች ጠቅላላ ድምር ሠላሳ ሰባት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የዳ​ዊት ኀያ​ላ​ንም ስማ​ቸው ይህ ነው። የኢ​ዮ​አብ ወን​ድም አሣ​ሄል በሠ​ላ​ሳው መካ​ከል ነበረ፤ የቤተ ልሔም ሰው የአ​ጎቱ የዱዲ ልጅ ኤል​ያ​ናን፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የኢዮአብም ወንድም አሣሄል በሠላሳው መካከል ነበረ፥ የቤተ ልሔም ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፥

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 23:24
6 Referencias Cruzadas  

እነርሱንም የጽሩያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ሰዎች ወጥተው በገባዖን ኲሬ አጠገብ ተገናቿቸው፤ አንዱ ወገን በኲሬው ወዲህ ማዶ፥ ሌላው ወገን ደግሞ በኲሬው ወዲያ ማዶ ተቀመጠ።


ሦስቱ የጽሩያ ልጆች ኢዮአብ፥ አቢሳና አሣሄል እዚያው ነበሩ። አሣሄል እንደ ዱር ሚዳቋ በሩጫ ፈጣን ነበረ፤


ጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በተደረገ ሌላ ጦርነትም፥ የቤተልሔሙ የያዒር ዓርጊምን ልጅ ኤልሐናን፥ የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን የጌት ሰው ጎልያድን ገደለው።


ከሠላሳዎቹ ይልቅ የከበረ ሰው ነበረ፤ ነገር ግን ከሦስቱ እንደ አንዱ አልነበረም። ዳዊትም የክብር ዘበኞቹ አለቃ አድርጎ ሾመው።


ደግሞም በሠራዊቱ ዘንድ የነበሩት ኃያላን እነዚህ ናቸው፤ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፥ የቤተልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፥


ለአራተኛው ወር አራተኛው አለቃ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፥ ከእርሱም በኋላ ልጁ ዝባድያ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ውስጥ ሀያ አራት ሺህ አባላት ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos