ከሠላሳውም አለቆች ሦስቱ ወርደው ወደ ቃሶን ወደ ዳዊት ወደ አዶላም ዋሻ መጡ፤ የፍልስጥኤማውያንም ጭፍራ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።
2 ሳሙኤል 23:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ከሦስቱ ይልቅ የከበረ ነበር፤ አለቃቸውም ሆነ፤ ነገር ግን ወደ ሦስቱ አልደረሰም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቢሳ ከሦስቱ ይልቅ እጅግ የከበረ አልነበረምን? ከእነርሱ እንደ አንዱ ባይሆንም አለቃቸው ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ከሠላሳው ይልቅ እጅግ ዝነኛ ስለ ነበር፤ አለቃቸው ሆኖ ነበር፥ ነገር ግን ወደ ሦስቱ ደረጃ አልደረሰም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሠላሳዎቹ መካከል እጅግ ዝነኛ በመሆኑም የእነርሱ አለቃ ሆነ፤ ይሁን እንጂ የሦስቱን ጀግኖች ያኽል ዝነኛ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ በሠላሳው መካከል የከበረ አልነበረምን? ስለዚህም አለቃቸው ሆኖ ነበር፥ ነገር ግን ወደ ሦስቱ አልደረሰም። |
ከሠላሳውም አለቆች ሦስቱ ወርደው ወደ ቃሶን ወደ ዳዊት ወደ አዶላም ዋሻ መጡ፤ የፍልስጥኤማውያንም ጭፍራ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።
ሦስቱም ኀያላን የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ሰንጥቀው ሄዱ፤ በበሩም አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ቀዱ፤ ይዘውም ለዳዊት አመጡለት፤ እርሱ ግን ሊጠጣ አልወደደም፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር አፈሰሰው።
የሶርህያም ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበር። እርሱም ጦሩን በሦስቱ መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፤ ስሙም በሦስቱ ዘንድ ተጠርቶ ነበር።
በቀበስሄል የነበረው ታላቅ ሥራ ያደረገው የዮዳሄ ልጅ በናያስ የሞዓባዊውን የአርኤልን ሁለት ልጆች ገደለ፤ በአመዳዩም ወራት ወርዶ በጕድጓድ ውስጥ አንበሳ ገደለ።
ከእርሱም በኋላ የዳዊት የአጎቱ ልጅ የዱዲ ልጅ ኤልያናን ነበረ፤ ለሰልፍ የተሰበሰቡትን ፍልስጥኤማውያንን በተገዳደሩ ጊዜ ከዳዊት ጋር ከነበሩ ከሦስቱ ኀያላን አንዱ እርሱ ነበረ፤ የእስራኤልም ሰዎች ተመለሱ።
እነሆ፥ ከሠላሳው ይልቅ የከበረ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ ፊተኞቹ ወደ ሦስቱ አልደረሰም። ዳዊትም በናያስን በሀገሩ ላይ ሾመው።
በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል፤ አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል።”
የፀሐይ ክብሩ ሌላ ነው፤ የጨረቃም ክብሩ ሌላ ነው፤ የከዋክብትም ክብራቸው ሌላ ነው፤ ኮከብ ከኮከብ በክብር ይበልጣልና።