Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 15:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 የፀ​ሐይ ክብሩ ሌላ ነው፤ የጨ​ረ​ቃም ክብሩ ሌላ ነው፤ የከ​ዋ​ክ​ብ​ትም ክብ​ራ​ቸው ሌላ ነው፤ ኮከብ ከኮ​ከብ በክ​ብር ይበ​ል​ጣ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 የፀሓይ ክብር አንድ ዐይነት ነው፤ የጨረቃ ክብር ሌላ ነው፤ የከዋክብት ደግሞ ሌላ ነው፤ የአንዱም ኮከብ ክብር ከሌላው ኮከብ ክብር ይለያል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 የፀሓይ ክብር አንድ ነው፤ የጨረቃ ክብር ሌላ ነው፤ የከዋክብት ደግሞ ሌላ ነው፤ የአንዱም ኮከብ ክብር ከሌላው ኮከብ ክብር ይለያል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 የፀሐይ ክብር አንድ ዐይነት ነው፤ የጨረቃ ክብር ሌላ ዐይነት ነው፤ የከዋክብትም ክብር ሌላ ዐይነት ነው፤ አንዱ ኮከብ ከሌላው ኮከብ የተለየ ክብር አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 የፀሐይ ክብር አንድ ነው የጨረቃም ክብር ሌላ ነው የከዋክብትም ክብር ሌላ ነው፤ በክብር አንዱ ኮከብ ከሌላው ኮከብ ይለያልና።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 15:41
10 Referencias Cruzadas  

ወደ ሰማይ አት​መ​ል​ከት፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕ​ዛብ ሁሉ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ፀሐ​ይ​ንና ጨረ​ቃን፥ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንና የሰ​ማ​ይን ሠራ​ዊት ሁሉ አይ​ተህ፥ ሰግ​ደ​ህ​ላ​ቸው፥ አም​ል​ከ​ሃ​ቸ​ውም እን​ዳ​ት​ስት ተጠ​ን​ቀቅ።


ጣራ​ቸው ይፈ​ር​ሳል፤ ግድ​ግ​ዳ​ቸ​ውም ይወ​ድ​ቃል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራ​ራና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ይነ​ግ​ሣ​ልና፥ በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹም ፊት ይከ​ብ​ራ​ልና።


የጣ​ቶ​ች​ህን ሥራ ሰማ​ዮ​ችን፥ አንተ የሠ​ራ​ሃ​ቸ​ውን፥ ጨረ​ቃ​ንና ከዋ​ክ​ብ​ትን እና​ያ​ለ​ንና።


የሚ​ያ​በራ ፀሐይ እን​ደ​ሚ​ጠፋ ጨረ​ቃም እን​ደ​ም​ት​ጨ​ልም አላ​ይ​ምን? በራ​ሳ​ቸው ለመ​ኖር ኀይል የላ​ቸ​ው​ምና፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “በም​ድር ላይ ያበሩ ዘንድ፥ በቀ​ንና በሌ​ሊ​ትም ይለዩ ዘንድ ብር​ሃ​ናት በሰ​ማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለም​ል​ክ​ቶች፥ ለዘ​መ​ናት፥ ለዕ​ለ​ታት፥ ለዓ​መ​ታ​ትም ይሁኑ።


ሰማ​ያዊ አካል አለ፤ ምድ​ራዊ አካ​ልም አለ፤ ነገር ግን በሰ​ማይ ያለው አካል ክብሩ ልዩ ነው፤ በም​ድ​ርም ያለው አካል ክብሩ ልዩ ነው።


የሙ​ታን ትን​ሣ​ኤ​ያ​ቸው እን​ዲሁ ነው፥ በሚ​ፈ​ርስ አካል ይዘ​ራል፤ በማ​ይ​ፈ​ርስ አካል ይነ​ሣል።


እር​ሱ​ንም፦ አን​ተም በአ​ም​ስት ከተ​ሞች ተሾም አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios