2 ሳሙኤል 22:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሞት ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድም ደረሰብኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤ የሞት ወጥመድም ተጋረጠብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሲኦል ገመድ ተበተበኝ፤ የሞትም ወጥመድ ተጋረጠብኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሲኦል ገመድ ተበተበኝ፤ የሞት ወጥመድም ተጠመደብኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሲኦል ጣር ከበበኝ፥ የሞት ወጥመድ ደረሰብኝ። |
በጽድቅ ገሥጸኝ፥ በምሕረትም ዝለፈኝ፥ የኀጢአተኛ ዘይትን ግን ራሴን አልቀባም፤ ዳግመኛም ጸሎቴ ይቅር እንዳትላቸው ነውና።
በፀሐይ ውስጥ ድንኳኑን አደረገ፥ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፤ በመንገዱ እንደሚራመድ አርበኛ ደስ ይለዋል።