2 ሳሙኤል 22:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተመረጠም ጋር የተመረጠ ትሆናለህ፤ ከጠማማ ጋርም ጠማማ ትሆናለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ መሆንህን፣ ለጠማማ ሰው ግን አንተም ጠማማ መሆንህን ታሳያለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ ሆነህ ትታያለህ፥ ለጠማማ ሰው ግን ጠማማ ሆነህ ትታያለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለንጹሖች ንጹሕ ነህ፤ ለጠማሞች ግን ተገቢ ዋጋቸውን ትሰጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፥ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ። |
“እንደ ሸክላ ሠሪ ሥራ ውብ አድርጌ ሠራሁህ፤ ምድርን የሚያርስ ሁልጊዜ ያርሳልን? ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? እጅ የለህምና መሥራት አትችልም ይለዋልን? ጭቃ ሠሪውን ይከራከረዋልን?
እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱ መጠን እንዲሁ እግዚአብሔር ይህን የማይገባውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእምሮን ሰጣቸው።