2 ሳሙኤል 22:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አለ፥ “እግዚአብሔር ዓለቴ፥ አምባዬም፥ መድኀኒቴም ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አለ፤ ጌታ ዐለቴ ዐምባዬና ታዳጊዬ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አለቴ፥ አምባዬ የደኅንነቴ ኀይል፥ ጠንካራ ምሽጌ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ዓለቴ አምባዬ መድኃኒቴ ነው፥ |
የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤ የእስራኤልም ጠባቂ በምሳሌ እንዲህ አለኝ፦ “እግዚአብሔርን መፍራት ታጸኑ ዘንድ፥ በሰዎች መካከል ተናገርሁ፥”
እግዚአብሔር በሥራው እውነተኛ ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ እግዚአብሔር የታመነ ነው፤ ክፋትም የለበትም፤ እግዚአብሔር ጻድቅና ቸር ነው።
ሳኦልና ሰዎቹም ሊፈልጉት ሄዱ፤ ለዳዊትም ነገሩት፤ እርሱም በማዖን ምድረ በዳ ወዳለው ዓለት ወረደ፤ ሳኦልም ያን በሰማ ጊዜ ዳዊትን በማዖን ምድረ በዳ ተከትሎ አሳደደው።