ኢዮአብም ሕዝቡን ስለ ራራላቸው መለከት አስነፋ፤ ሕዝቡም እስራኤልን ተከትለው እንዳያሳድዱአቸው መለሳቸው።
2 ሳሙኤል 20:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያቺም ሴት ወደ ሕዝቡ ሁሉ ገብታ ለከተማው ሕዝብ ሁሉ በብልሀት ነገረቻቸው፤ የቢኮሪን ልጅ የሳቡሄን ራስ ቈርጠው ሰጡአት፤ ወደ ኢዮአብም ጣለችው። ኢዮአብም መለከቱን ነፋ፤ ሰውም ሁሉ ከከተማዪቱ ርቆ እያንዳንዱ ወደ ድንኳኑ ሄደ። ኢዮአብም ወደ ንጉሡ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም በኋላ ሴቲቱ ብልኅነት የተሞላበት ምክሯን ይዛ ወደ ሕዝቡ ሁሉ ሄደች፤ እነርሱም የቢክሪን ልጅ የሳቤዔን ራስ ቈርጠው ለኢዮአብ ወረወሩለት፤ ስለዚህ ኢዮአብ መለከቱን ነፋ፤ ሰዎቹም ከከተማዪቱ ርቀው በየአቅጣጫው ተበታተኑ፤ እያንዳንዳቸውም ወደ የቤታቸው ሄዱ፤ ኢዮአብም ወደ ንጉሡ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ሴቲቱ ብልኅ ምክሯን ይዛ ወደ ሕዝቡ ሁሉ ሄደች፤ እነርሱም የቢክሪን ልጅ የሼባዕን ራስ ቆርጠው ለኢዮአብ ወረወሩለት፤ ስለዚህ ኢዮአብ መለከቱን ነፋ፤ ሰዎቹም ከከተማዪቱ ርቀው በየአቅጣጫው ተበታተኑ፤ እያንዳንዳቸውም ወደየቤታቸው ሄዱ፤ ኢዮአብም ወደ ንጉሡ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ዕቅድ በተግባር ለመግለጥ ወደ ከተማይቱ ሕዝብ ሄደች፤ እነርሱም የቢክሪን ልጅ የሺባዕን ራስ ቈርጠው በግንቡ ላይ ለኢዮአብ ወረወሩለት፤ እርሱም ወታደሮቹ ከተማይቱን ለቀው ይወጡ ዘንድ ምልክት እንዲሆን እምቢልታ ነፋ፤ እነርሱም ወደየቤታቸው ተመለሱ፤ ኢዮዓብም ንጉሡን ለማግኘት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም በልሃትዋ ወደ ሕዝቡ ሁሉ ሄደች፥ እነርሱም የቢክሪን ልጅ የሳቤዔን ራስ ቆርጠው ወደ ኢዮአብ ጣሉት። እርሱም ቀንደ መለከቱን ነፋ፥ ሰውም ሁሉ ከከተማይቱ ርቆ እያንዳንዱ ወደ ድንኳኑ ሄደ። ኢዮአብም ወደ ንጉሡ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። |
ኢዮአብም ሕዝቡን ስለ ራራላቸው መለከት አስነፋ፤ ሕዝቡም እስራኤልን ተከትለው እንዳያሳድዱአቸው መለሳቸው።
አቤሴሎምንም ወስዶ በበረሓ ባለ በታላቅ ገደል ውስጥ ጣለው፤ እጅግም ታላቅ የሆነ የድንጋይ ክምር ከመረበት፤ እስራኤልም ሁሉ ሸሽተው ወደ ድንኳናቸው ገቡ።
ኢዮአብም ቀንደ መለከት ነፋ፤ ሕዝቡም ሁሉ ተመለሰ፤ ከዚያም በኋላ እስራኤልን አላሳደዱአቸውም፤ ደግመውም አልተዋጉም።
በዚያም አንድ ብንያማዊ የቢኮሪ ልጅ ስሙ ሳቡሄ የሚባል የዐመፅ ልጅ የሆነ ሰው ነበረ፤ እርሱም፥ “ከዳዊት ዘንድ እድል ፋንታ የለንም፦ ከእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፥ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ” ብሎ መለከት ነፋ።
ከቅጥሩም አንዲት ብልሃተኛ ሴት፥ “ስሙ፥ ስሙ፥ ኢዮአብንም፦ እነግርህ ዘንድ ወደዚህ ቅረብ በሉት” ስትል ጮኸች። ወደ እርስዋም ቀረበ፤
ክፉን ከሚያደርጉ ወገን ፈጥኖ ክርክርን የሚያደርግ የለምና፤ ስለዚህ የሰው ልጆች ልብ በእነርሱ ክፉን ለመሥራት ጠነከረ።