La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 20:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሴቲ​ቱም፥ “ኢዮ​አብ አንተ ነህን?” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “እኔ ነኝ” ብሎ መለ​ሰ​ላት። እር​ስ​ዋም፥ “የባ​ሪ​ያ​ህን ቃል ስማ” አለ​ችው። ኢዮ​አ​ብም፥ “እሰ​ማ​ለሁ” አላት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢዮአብ ወደ እርሷ ሄደ፤ እርሷም፣ “ኢዮአብ አንተ ነህ?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም፣ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰላት። እርሷም፣ “እንግዲህ አገልጋይህ የምትለውን ስማ” አለችው። እርሱም፣ “ዕሺ፣ አደምጣለሁ” አላት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢዮአብ ወደ እርሷ ቀረበ፤ እርሷም፥ “ኢዮአብ አንተ ነህ?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም፥ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰላት። እርሷም፥ “እንግዲህ አገልጋይህ የምትለውን አድምጥ” አለችው። እርሱም፥ “እያዳመጥኩ ነው” አላት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢዮአብ ወደዚያ በሄደ ጊዜም ሴትዮዋ “ኢዮአብ የምትባለው አንተ ነህን?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም “አዎ እኔ ነኝ” አላት። እርስዋም “ጌታዬ፥ እስቲ አድምጠኝ” አለችው፤ እርሱም “እነሆ፥ አዳምጥሻለሁ” አላት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ እርስዋም ቀረበ፥ ሴቲቱም፦ ኢዮአብ አንተ ነህን? አለች። እርሱም፦ እኔ ነኝ ብሎ መለሰላት። እርስዋም፦ የባሪያህን ቃል ስማ አለችው። እርሱም፦ እሰማለሁ አላት።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 20:17
4 Referencias Cruzadas  

ሴቲ​ቱም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ለጌ​ታዬ ለን​ጉሥ አንድ ቃል ልና​ገር” አለች፤ እር​ሱም፥ “ተና​ገሪ” አላት።


ከቅ​ጥ​ሩም አን​ዲት ብል​ሃ​ተኛ ሴት፥ “ስሙ፥ ስሙ፥ ኢዮ​አ​ብ​ንም፦ እነ​ግ​ርህ ዘንድ ወደ​ዚህ ቅረብ በሉት” ስትል ጮኸች። ወደ እር​ስ​ዋም ቀረበ፤


እር​ስ​ዋም እን​ዲህ አለች፥ “የቀ​ደሙ ሰዎች በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አማ​ኞች በሚ​ያ​ስ​ቡት ነገር ተሳ​ስ​ተው እንደ ሆነ በአ​ቤ​ልና በዳን በእ​ው​ነት ይጠ​ይቁ ይባል ነበር፤ በር​ግ​ጥም በዚህ ዐይ​ነት ነገር ከተ​ሳ​ሳቱ በአ​ቤል ይጠ​ይቁ ነበር።


በእ​ግ​ሩም ላይ ወደ​ቀች፤ እን​ዲ​ህም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! ይህ ኀጢ​ኣት በእኔ ላይ ይሁን፤ እኔ ባሪ​ያህ በጆ​ሮህ ልና​ገር፥ የባ​ሪ​ያ​ህ​ንም ቃል አድ​ምጥ።