አሜሳይም በደም ተነክሮ በመንገድ መካከል ወድቆ ነበር፤ ያም ሰው ወደ እርሱ የሚመጣ ሁሉ ሲቆም አይቶአልና ሕዝቡ ሁሉ እንደ ቆመ ባየ ጊዜ አሜሳይን ከመንገድ ላይ ወደ እርሻ ውስጥ ፈቀቅ አደረገው፤ በልብስም ከደነው።
2 ሳሙኤል 20:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኢዮአብም ብላቴኖች አንዱ በአሜሳይ ሬሳ አጠገብ ቆሞ፥ “ኢዮአብ የሚፈልገው ምንድን ነው? የዳዊትም የሆኑ ኢዮአብን የሚከተሉ እነማን ናቸው?” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአሜሳይ ሬሳ አጠገብ ከቆሙት ከኢዮአብ ሰዎች አንዱ፤ “ኢዮአብን የሚወድድ፣ የዳዊትም የሆነ ሁሉ ኢዮአብን ይከተል!” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአማሳይ ሬሳ አጠገብ ከቆሙት ከኢዮአብ ሰዎች አንዱ፤ “ኢዮአብን የሚወድ፥ የዳዊትም የሆነ ሁሉ ኢዮአብን ይከተል!” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኢዮአብ ወታደሮች አንዱ በዐማሳ ሬሳ አጠገብ ቆሞ “ኢዮአብንና ዳዊትን የምትከተሉ ሁሉ ኢዮአብን ተከተሉ!” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ የቢክሪን ልጅ ሳቤዔን አሳደዱ። ከኢዮአብም ብላቴኖች አንዱ በአሜሳይ ሬሳ አጠገብ ቆሞ፦ ለኢዮአብ ወዳጅ የሚሆን ለዳዊትም የሆነ ሁሉ ኢዮአብን ይከተል ይል ነበር። |
አሜሳይም በደም ተነክሮ በመንገድ መካከል ወድቆ ነበር፤ ያም ሰው ወደ እርሱ የሚመጣ ሁሉ ሲቆም አይቶአልና ሕዝቡ ሁሉ እንደ ቆመ ባየ ጊዜ አሜሳይን ከመንገድ ላይ ወደ እርሻ ውስጥ ፈቀቅ አደረገው፤ በልብስም ከደነው።
ነገሩ እንዲህ አይደለም፤ ከተራራማው ከኤፍሬም ሀገር የሚሆን የቢኮሪ ልጅ ሳቡሄ የሚባል አንድ ሰው ግን በንጉሡ በዳዊት ላይ እጁን አነሣ፤ እርሱን ብቻውን ስጡኝ፤ እኔም ከከተማዪቱ እርቃለሁ” አላት። ሴቲቱም ኢዮአብን፥ “እነሆ፥ ራሱ ከቅጥር ላይ ይጣልልሃል” አለችው።
ፊቱንም አቅንቶ በመስኮቱ አያት። “አንቺ ማን ነሽ? ወደዚህ ወደ እኔ ውረጂ” አላት። ከዚህም በኋላ ሁለት ጃንደረቦች ወደ እርሱ ተመለከቱ።