ኢዮአብም አበኔርን ከማሳደድ ተመለሰ፤ ሕዝቡንም ሁሉ ሰበሰበ፤ የዳዊትንም ብላቴኖች አስቈጠራቸው፤ የሞቱትም ሰዎች ከአሣሄል ሌላ ዐሥራ ዘጠኝ ሰዎች ናቸው።
2 ሳሙኤል 2:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳዊትም ብላቴኖች ከብንያም እና ከአበኔር ሰዎች ሦስት መቶ ስድሳ ሰዎችን ገደሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳዊት ሰዎች ግን ከአበኔር ጋራ ከነበሩት ሦስት መቶ ስድሳ ብንያማውያን ገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊት አገልጋዮች ግን ከአበኔር ጋር ከነበሩት ሦስት መቶ ሥልሳ ብንያማውያን ገደሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዳዊት ሰዎች የብንያም ነገድ ከሆኑት ከአበኔር ተከታዮች ሦስት መቶ ሥልሳ ሰዎችን ገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊትም ባሪያዎች ከብንያምና ከአበኔር ሰዎች ሦስት መቶ ስድሳ ያህል ገደሉ። |
ኢዮአብም አበኔርን ከማሳደድ ተመለሰ፤ ሕዝቡንም ሁሉ ሰበሰበ፤ የዳዊትንም ብላቴኖች አስቈጠራቸው፤ የሞቱትም ሰዎች ከአሣሄል ሌላ ዐሥራ ዘጠኝ ሰዎች ናቸው።
አሣሄልንም አንሥተው በቤተ ልሔም በአባቱ መቃብር ቀበሩት፤ ኢዮአብና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ፤ ሄዱ፥ በኬብሮንም አነጉ።
በሳኦል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል ለብዙ ጊዜ ጦርነት ሆነ፤ የዳዊት ቤት እየበረታ፥ የሳኦል ቤት ግን እየደከመ የሚሄድ ሆነ።
በከተማውም የተቀመጡት የከተማው ሰዎችና ሽማግሌዎች፥ አለቆችም ኤልዛቤል እንዳዘዘቻቸውና ወደ እነርሱ በተላከው ደብዳቤ እንደ ተጻፈው እንዲሁ አደረጉ።