ኢዮአብም ሕዝቡን ስለ ራራላቸው መለከት አስነፋ፤ ሕዝቡም እስራኤልን ተከትለው እንዳያሳድዱአቸው መለሳቸው።
2 ሳሙኤል 2:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም ቀንደ መለከት ነፋ፤ ሕዝቡም ሁሉ ተመለሰ፤ ከዚያም በኋላ እስራኤልን አላሳደዱአቸውም፤ ደግመውም አልተዋጉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ኢዮአብ ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ ከዚያም በኋላ ሰዎቹ በሙሉ እስራኤልን ማሳደዱን ተው፤ ውጊያውም በዚሁ አበቃ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ኢዮአብ ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ ከዚያም በኋላ ሰዎቹ በሙሉ እስራኤልን ማሳደዱን ተዉ ውጊያውንም አቆሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢዮአብ እምቢልታውን ነፋ፤ ሰዎችም ሁሉ ቆሙ፤ ከዚያ በኋላ እስራኤልን አላሳደዱም፤ ጦርነቱንም አልቀጠሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም ቀንደ መለከት ነፋ፥ ሕዝቡም ሁሉ ቆመ፥ ከዚያም በኋላ እስራኤልን አላሳደደም፥ ሰይፍም አላደረገም። |
ኢዮአብም ሕዝቡን ስለ ራራላቸው መለከት አስነፋ፤ ሕዝቡም እስራኤልን ተከትለው እንዳያሳድዱአቸው መለሳቸው።
ያቺም ሴት ወደ ሕዝቡ ሁሉ ገብታ ለከተማው ሕዝብ ሁሉ በብልሀት ነገረቻቸው፤ የቢኮሪን ልጅ የሳቡሄን ራስ ቈርጠው ሰጡአት፤ ወደ ኢዮአብም ጣለችው። ኢዮአብም መለከቱን ነፋ፤ ሰውም ሁሉ ከከተማዪቱ ርቆ እያንዳንዱ ወደ ድንኳኑ ሄደ። ኢዮአብም ወደ ንጉሡ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
በሳኦል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል ለብዙ ጊዜ ጦርነት ሆነ፤ የዳዊት ቤት እየበረታ፥ የሳኦል ቤት ግን እየደከመ የሚሄድ ሆነ።
ዮናታንም በኮረብታው የነበሩትን የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ያን ሰሙ፤ ሳኦልም፦ እስራኤል ይስሙ ብሎ በሀገሩ ሁሉ ቀንደ መለከት ነፋ።