2 ሳሙኤል 19:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳም ሰዎች ሁሉ ለእስራኤል ሰዎች መልሰው፥ “ንጉሡ ለእኛ ቅርባችን ነው፤ ስለምን በዚህ ነገር ትቈጣላችሁ? በውኑ ከንጉሡ አንዳች በልተናልን? ወይስ እርሱ በረከት ሰጥቶናልን? ወይስ ጭፍራ አድርጎ ሾመንን?” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳም ሰዎች ሁሉ፣ ለእስራኤል ሰዎች፣ “ይህን ያደረግነው ንጉሡ የቅርብ ዘመዳችን ስለ ሆነ ነው፤ ታዲያ ይህ እናንተን የሚያስቈጣ ነው? እኛ ከንጉሡ ተቀብለን አንዳች በልተናልን? ለራሳችንስ ምን የወሰድነው ነገር አለ?” አሏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዲያውም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ መጥተው፥ “ወንድሞቻችን የይሁዳ ሰዎች ንጉሡን በሹልክታ ለብቻቸው ይዘው እርሱንና ቤተሰቡን ከተከታዮቹ ጋር ዮርዳኖስን ለምን አሻገሩ?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳም ሰዎች “እኛ ይህን ያደረግነው ንጉሡ የእኛ ወገን ስለ ሆነ ብቻ ነው፤ ታዲያ፥ እናንተስ በዚህ ነገር ስለምን ትቈጣላችሁ? እርሱ ለምግባችን ምንም የከፈለን ነገር የለም፤ ሌላም ምንም ነገር አልሰጠንም” ሲሉ መለሱላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳም ሰዎች ሁሉ ለእስራኤል ሰዎች መልሰው፦ ንጉሡ ለእኛ ቅርባችን ነው፥ ስለ ምን በዚህ ነገር ትቆጣላችሁ? በውኑ ከንጉሡ አንዳች በልተናልን? ወይስ እርሱ በረከት ሰጥቶናልን? አሉ። |
የእስራኤልም ሰዎች ለይሁዳ ሰዎች መልሰው፥ “በንጉሡ ዘንድ ለእኛ ዐሥር ክፍል አለን፤ ከእናንተም እኛ እንቀድማለን፤ እኛም በኵር ነን፤ ለዳዊትም ከእናንተ እኛ እንቀርባለን፤ ስለምን ናቃችሁን? ንጉሡንስ እንመልሰው ዘንድ ከእናንተ የእኛ ቃል አይቀድምምን?” አሏቸው። የይሁዳም ሰዎች ቃል ከእስራኤል ሰዎች ቃል ይልቅ ጠነከረ።
የይሁዳም ሰዎች መጥተው በይሁዳ ቤት ይነግሥ ዘንድ ዳዊትን በዚያ ቀቡት። ሳኦልን የቀበሩት የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ናቸው ብለው ለዳዊት ነገሩት።
የኤፍሬም ሰዎችም፥ “ይህ ያደረግህብን ምንድን ነው? ምድያምን ለመዋጋት በወጣህ ጊዜ ለምን አልጠራኸንም?” አሉት። ጽኑ ጥልም ተጣሉት።