ባልዋም እያለቀሰ ከእርስዋ ጋር ሄደ፤ እስከ ብራቂም ድረስ ተከተላት። አበኔርም፥ “ሂድ፤ ተመለስ” አለው፤ እርሱም ተመለሰ።
2 ሳሙኤል 19:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከባውሪም ሀገር የነበረው የኢያሚን ልጅ የጌራ ልጅ ሳሚም ከይሁዳ ሰዎች ጋር ንጉሥ ዳዊትን ሊቀበል ፈጥኖ ወረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባሑሪም ሰው የሆነው የጌራ ልጅ ብንያማዊው ሳሚ ከይሁዳ ሰዎች ጋራ ሆኖ ንጉሥ ዳዊትን ለመቀበል ፈጥኖ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ተመልሶ እስከ ዮርዳኖስ ድረስ መጣ። የይሁዳም ሰዎች ንጉሡን ተቀብለው ዮርዳኖስን ለማሻገር እስከ ጌልገላ ድረስ መጥተው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያኑ ጊዜም የባሑሪም ተወላጅ የሆነው የጌራ ልጅ ብንያማዊው ሺምዒ ከይሁዳ ሰዎች ጋር ንጉሥ ዳዊትን ለመቀበል ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ፈጥኖ ሄደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብራቂምም አገር የነበረው ብንያማዊው የጌራ ልጅ ሳሚ ከይሁዳ ሰዎች ጋር ዳዊትን ሊቀበል ፈጥኖ ወረደ። |
ባልዋም እያለቀሰ ከእርስዋ ጋር ሄደ፤ እስከ ብራቂም ድረስ ተከተላት። አበኔርም፥ “ሂድ፤ ተመለስ” አለው፤ እርሱም ተመለሰ።
የባውሬም ሀገር ሰው የብንያማዊው የጌራ ልጅ ሳሚ እነሆ! በአንተ ዘንድ ነው፤ እኔም ወደ መሃናይም በሄድሁ ጊዜ ብርቱ ርግማን ረገመኝ፤ ከዚያም በኋላ ዮርዳኖስን በተሻገርሁ ጊዜ ሊቀበለኝ ወረደ፤ እኔም፦ ‘በሰይፍ አልገድልህም’ ብዬ በእግዚአብሔር ምየለታለሁ።
በፊቴም ወደ ጌልገላ ትወርዳለህ፤ እኔም እነሆ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀርብ ዘንድ፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት እሠዋ ዘንድ ወደ አንተ እወርዳለሁ፤ እኔ ወደ አንተ እስክመጣና የምታደርገውን እስከምነግርህ ድረስ ሰባት ቀን ትቈያለህ።”