አቤሴሎምም ኰበለለ። ጕበኛውም ጐልማሳ ዐይኑን ከፍ አደረገ፤ እነሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋላው በተራራው አጠገብ በመንገድ ሲመጡ አየ። ጕበኛውም መጥቶ ለንጉሡ እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ብዙ ሰዎች በተራራው ጎን ባለው በአርኖን መንገድ ሲመጡ አየሁ።”
2 ሳሙኤል 18:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በሁለት በር መካከል ተቀምጦ ነበር፤ ዘበኛውም በቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ወጣ፤ ዐይኑንም አቅንቶ ብቻውን የሚሮጥ ሰው አየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ሳለ፣ ጠባቂው ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጥቶ ወደ ውጭ ሲመለከት፣ አንድ ሰው ብቻውን ሲሮጥ አየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ነበር፤ ጠባቂውም ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጣ፤ ቀና ብሎም ሲመለከት አንድ ሰው ብቻውን እየሮጠ ሲመጣ አየ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት በከተማይቱ ውስጣዊና ውጫዊ በሮች መካከል ባለው ግልጥ ቦታ ተቀምጦ ነበር፤ ጠባቂው በቅጥሩ በኩል ወደ ማማው ወጥቶ ስለ ነበር ቀና ብሎ ሲመለከት አንድ ሰው ብቻውን እየሮጠ ሲመጣ አየ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በሁለት በር መካከል ተቀምጦ ነበር፥ ዘበኛውም በቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደበሩ ሰገነት ወጣ፥ አይኑንም አቅንቶ ብቻውን የሚሮጥ ሰው አየ። |
አቤሴሎምም ኰበለለ። ጕበኛውም ጐልማሳ ዐይኑን ከፍ አደረገ፤ እነሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋላው በተራራው አጠገብ በመንገድ ሲመጡ አየ። ጕበኛውም መጥቶ ለንጉሡ እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ብዙ ሰዎች በተራራው ጎን ባለው በአርኖን መንገድ ሲመጡ አየሁ።”
እርሱም፥ “እኔ ብሮጥ ምን ይገድዳል?” አለ። እርሱም፥ “ሩጥ” አለው። አኪማሖስም በሰርጥ ጎዳና በኩል ሮጠ፤ ኩሲንም ቀደመው።
ንጉሡም፥ “በፊታችሁ መልካም የሚመስላችሁን አደርጋለሁ” አላቸው። ንጉሡም በበሩ አጠገብ ቆመ፤ ሕዝቡም ሁሉ መቶ በመቶ፥ ሺህ በሺህ እየሆኑ ወጡ።
ንጉሡም ተነሥቶ በበሩ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ ንጉሡ በበሩ ተቀምጧል ብለው ተናገሩ፤ ሕዝቡም ሁሉ በበሩ ወደ ንጉሡ ፊት ወጡ። እስራኤልም እያንዳንዱ ወደ ድንኳኑ ሸሽቶ ገብቶ ነበር።
በመጣም ጊዜ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ልቡ ተናውጦ ነበርና በመንገድ ዳር በወንበሩ ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር፤ ሰውዬውም ወደ ከተማዪቱ ገብቶ ባወራ ጊዜ ከተማዪቱ ሁሉ ተጭዋጭዋኸች።